Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 10:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አዝ​ዞ​ኛ​ልና፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከእ​ሳት ቍር​ባን ለአ​ን​ተም፥ ለል​ጆ​ች​ህም የተ​ሰጠ ሥር​ዐት ነውና በቅ​ዱስ ስፍራ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው መሥዋዕት ያንተና የልጆችህ ድርሻ ይህ ስለ ሆነ፣ በተቀደሰ ስፍራ ብሉት፤ እንዲህ ታዝዣለሁና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ለጌታም ከሆነው በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ለአንተም ለልጆችህም የተሰጠ ድርሻ ነውና በቅዱስ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤ ይህንንም እንዲህ ታዝዣለሁና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው የምግብ መባ ተከፍሎ ለአንተና ለልጆችህ የተመደበ ድርሻ ስለ ሆነ በተቀደሰ ስፍራ ብሉት። ይህን እንድታደርጉ እግዚአብሔር አዞኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ለእግዚአብሔር ከሆነው ከእሳት ቍርባን ለአንተም ለልጆችህም የተሰጠ ሥርዓት ነውና በቅዱስ ስፍራ ትበሉታላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 10:13
7 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በልዩ ስፍራ አን​ጻር በሰ​ሜ​ንና በደ​ቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነ​ርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ካህ​ናቱ ከሁሉ ይልቅ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ምግብ የሚ​በ​ሉ​ባ​ቸው ቤቶች ናቸው። ስፍ​ራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር፥ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንና የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት ያኖ​ራሉ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ የተ​ረ​ፉ​ለ​ትን ልጆ​ቹን አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን አላ​ቸው፥ “ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከእ​ሳት ቍር​ባን የቀ​ረ​ውን የስ​ን​ዴ​ውን ቍር​ባን ውሰዱ፤ ቂጣም አድ​ር​ጋ​ችሁ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ብሉት፤


እነ​ዚ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ሥር​ዐት እን​ዲ​ሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ፍር​ም​ባና ወርች አንተ፥ ከአ​ንተ ጋርም ልጆ​ችህ፥ ቤተ​ሰ​ብ​ህም ተለ​ይቶ በን​ጹሕ ስፍራ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም የተ​ረ​ፈው ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሆ​ናል፤ ይህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የተ​ረፈ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


ከእ​ር​ሱም የተ​ረ​ፈ​ውን አሮ​ንና ልጆቹ ይበ​ሉ​ታል፤ ቂጣ ሆኖ በተ​ቀ​ደ​ሰው ስፍራ ይበ​ላል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ባለው አደ​ባ​ባይ ይበ​ሉ​ታል።


በቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳን ብሉት፤ ወን​ዶች ሁሉ ይብ​ሉት፤ አን​ተም ልጆ​ች​ህም ብሉት፤ ለአ​ንተ የተ​ቀ​ደሰ ነውና።


የተ​ቀ​ደሰ የሰው ነገር ሁሉ፥ ሰውም ለካ​ህኑ የሚ​ሰ​ጠው ሁሉ ለእ​ርሱ ይሁን።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos