ሰቈቃወ 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተከተለኝ፤ ጨረሰኝ፤ ባድማም አደረገኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመንገድ ጐትቶ አስወጣኝ፤ ቈራረጠኝም፤ ያለ ረዳትም ተወኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዴን ለወጠ፥ ገነጣጠለኝም፥ ባድማ አደረገኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመንገዴ አውጥቶ ገነጣጠለኝ፤ ብቸኛም አደረገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዴን ለወጠ፥ ገነጣጠለኝም፥ ባድማ አደረገኝ። |
ሰይፍን ለመግደል፥ ውሾችንም ለመጐተት፥ የሰማያትንም ወፎች፥ የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ይህችንም ከተማ ለጥፋትና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፤ በእርስዋም የሚያልፍ ሁሉ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ ይደነግጣል፤ ያፍዋጫልም።
እናንተም፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት፤ ለከለዳውያንም እጅ ተሰጥታለች በምትሉአት ምድር እርሻን እንደ ገና ይገዛሉ።
ስለዚህ ኀጢአታቸው በዝቶአልና፥ የዐመፃቸውም ብዛት ጸንቶአልና አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፤ የበረሃም ተኵላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፤ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።
ሜም። ከላይ እሳትን ሰደደ፤ አጥንቶችንም አቃጠለ፤ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም፤ ቀኑንም ሁሉ መከራ አጸናብኝ።
በመከራቸው ጊዜ በማለዳ ወደ እኔ ይገሰግሳሉ፤ እንዲህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናልና፥ እርሱም ይጠግነናል።
በዱር አራዊትም መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋም መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ እንዲሁ የያዕቆብ ቅሬታ በአሕዛብና በብዙ ወገኖች መካከል ይሆናል።
በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ “በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከባለ ጠግነትዋ የተነሣ ባለ ጠጋዎች ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና፤” እያሉ ጮኹ።