Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 3:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 የጌ​ጦ​ች​ሽም ሣጥ​ኖች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም፤ ብቻ​ሽ​ንም ትቀ​ሪ​ያ​ለሽ፤ ከም​ድ​ርም ጋር ትቀ​ላ​ቀ​ያ​ለሽ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የጽዮን ደጆች ያዝናሉ፣ ያለቅሳሉም፤ እርሷም ተረስታ በመሬት ላይ ትቀመጣለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የጽዮን ደጆች ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ እርሷም ተረስታ በመሬት ላይ ትቀመጣለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 የኢየሩሳሌም በሮች እርቃንዋን ሆና በልቅሶና በሐዘን እንደ ተቀመጠች ሴት ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በሮችዋ ያዝናሉ ያለቅሱማል፥ እርስዋም ብቻዋን በምድር ላይ ትቀመጣለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 3:26
19 Referencias Cruzadas  

ዮድ። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዝም ብለው በመ​ሬት ላይ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ትቢ​ያን በራ​ሳ​ቸው ላይ ነሰ​ነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና ደና​ግ​ሉን ወደ ምድር አወ​ረ​ዷ​ቸው።


ይሁዳ አለ​ቀ​ሰች፤ ደጆ​ች​ዋም ባዶ ሆኑ፤ በም​ድ​ርም ላይ ጨለሙ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎ​አል።


ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚ​መጣ የለ​ምና የጽ​ዮን መን​ገ​ዶች አለ​ቀሱ፤ በሮ​ችዋ ሁሉ ፈር​ሰ​ዋል፤ ካህ​ና​ቷም ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ደና​ግ​ሎ​ች​ዋም ተማ​ረኩ፤ እር​ስ​ዋም በም​ሬት አለች።


ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊ​ትም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​መጡ፤ ሕማሙ እጅግ አስ​ፈ​ሪና ታላቅ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ርሱ አንድ ቃል የሚ​ና​ገ​ረው አል​ነ​በ​ረም።


አን​ቺን ይጥ​ሉ​ሻል፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም ከአ​ንቺ ጋር ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ ድን​ጋ​ይ​ንም በደ​ን​ጋይ ላይ አይ​ተ​ዉ​ል​ሽም፤ የይ​ቅ​ር​ታ​ሽን ዘመን አላ​ወ​ቅ​ሽ​ምና።”


የባ​ሕ​ርም አለ​ቆች ሁሉ ከዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ይወ​ር​ዳሉ፤ ዘው​ዳ​ቸ​ውን ከራ​ሳ​ቸው ያወ​ር​ዳሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያወ​ል​ቃሉ፤ በመ​ሬ​ትም ላይ ተቀ​ም​ጠው ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ ሞታ​ቸ​ው​ንም ይፈ​ራሉ፤ ስለ አን​ቺም ያለ​ቅ​ሳሉ።


ቍስ​ሉ​ንም ያክ​ክ​በት ዘንድ ገል ወሰደ፥ ከከ​ተ​ማም ወጥቶ በአ​መድ ላይ ተቀ​መጠ።


አንቺ ድን​ግል የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በት​ቢ​ያም ላይ ተቀ​መጪ፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስ​ላ​ሳና ቅም​ጥል አት​ባ​ዪ​ምና ያለ ዙፋን በመ​ሬት ላይ ተቀ​መጪ።


‘እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ፤ ዋይ ዋይም አላላችሁም’ ይሉአቸዋል።


እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አለኝ፥ “ከተ​ሞች የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አጥ​ተው እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ ቤቶ​ችም ሰው አልቦ እስ​ኪ​ሆኑ፥ ምድ​ርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስ​ክ​ት​ቀር ድረስ ነው፤”


እና​ንተ የከ​ተ​ሞች በሮች ሆይ፥ ወዮ በሉ፤ እና​ን​ተም ከተ​ሞች ሆይ፥ ደን​ግጡ፥ ጩኹም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሆይ፥ ሁላ​ች​ሁም ቀል​ጣ​ች​ኋል፤ ጢስ ከሰ​ሜን ይወ​ጣ​ልና፥ እን​ግ​ዲ​ህም አት​ኖ​ሩ​ምና።


አር​ኤ​ል​ንም አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ፤ ይህ​ችም ኀይል፥ ይህ​ችም ብዕል የእኔ ትሆ​ና​ለች፥


ምድር አለ​ቀ​ሰች፤ ሊባ​ኖስ አፈረ፤ ሳሮ​ንም እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ገሊ​ላና ቀር​ሜ​ሎስ ታወቁ።


መበ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከባ​ሕር አሸዋ ይልቅ በዝ​ተ​ዋል፤ በብ​ላ​ቴ​ኖች እናት ላይ በቀ​ትር ጊዜ አጥ​ፊ​ውን አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ ጭን​ቀ​ት​ንና ድን​ጋ​ጤን በድ​ን​ገት አም​ጥ​ቼ​ባ​ታ​ለሁ።


አሌፍ። ሕዝብ ሞል​ቶ​ባት የነ​በ​ረች ከተማ ብቻ​ዋን እን​ዴት ተቀ​መ​ጠች! በአ​ሕ​ዛብ ተመ​ልታ የነ​በ​ረች እንደ መበ​ለት ሆና​ለች፤ አሕ​ዛ​ብን ትገዛ የነ​በ​ረች፥ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም ትገዛ የነ​በ​ረች ገባር ሆና​ለች።


ሔት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈ​ርስ ዘንድ ዐሰበ፤ የመ​ለ​ኪ​ያ​ው​ንም ገመድ ዘረጋ፤ እር​ስ​ዋን ከማ​ጥ​ፋት እጁን አል​መ​ለ​ሰም፤ ምሽ​ጉና ቅጥሩ አለ​ቀሱ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ደከሙ።


ሰዎች የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ይጠ​ፋሉ፤ ምድ​ሪ​ቱም ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”


ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።


የበ​ለ​ጸ​ገች ከተ​ማና ቤቶ​ችዋ ምድረ በዳ ይሆ​ናሉ። የከ​ተ​ማ​ውን ሀብ​ትና ያማሩ ቤቶ​ችን ይተ​ዋሉ፤ አን​ባ​ዎ​ችም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዋሻ፥ የም​ድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመ​ን​ጎ​ችም ማሰ​ማ​ሪያ ይሆ​ናሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios