እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ።
ኢያሱ 21:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ እነርሱም ምድሪቱን ወረሱ፣ መኖሪያቸውም አደረጓት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል የገባላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤላውያን ሰጠ። ምድሪቱንም ከወረሱ በኋላ በዚያ ተደላድለው ኖሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸው ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። |
እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ።
ስደተኛ ሆነህ የተቀመጥህባትን፥ እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጣትን ምድር ትወርስ ዘንድ የአባቴን የአብርሃምን በረከት ለአንተ ይስጥህ፤ ከአንተም በኋላ ለዘርህ።”
እነርሱም ወረሱአት፤ በከነዓን ምድር የሚኖሩትንም ሰዎች በፊታቸው አጠፋሃቸው፤ የሚወድዱትንም ነገር ያደርጉባቸው ዘንድ እነርሱንና ነገሥታቶቻቸውን፥ የምድሩንም አሕዛብ በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
ልቡም በፊትህ የታመነ ሆኖ አገኘኸው፤ የከነዓናዊውንና የኬጤዎናዊውን፥ የአሞሬዎናዊውንም፥ የፌርዜዎናዊውንም፥ የኢያቡሴዎናዊውንም፥ የጌርጌሴዎናዊውንም ምድር ለእርሱና ለዘሩ ትሰጥ ዘንድ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረግህ፤ አንተም ጻድቅ ነህና ቃልህን አጸናህ።
ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም ሀገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊዪቱና ወደ መልካሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም፤ በሕግህም አልሄዱም፤ ያደርጉም ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።
“የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ እነሆ እናንተ ወደ ከነዓን ምድር ትገባላችሁ፤ የከነዓንም ምድር ከአውራጃዎችዋ ጋር ለእናንተ ርስት ትሆናለች።
አምላካችሁ እግዚአብሔር በዕጣችሁ ለሁልጊዜ የሚሰጣችሁን ምድር ትገቡና ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፤ ትወርሱአታላችሁም፤ ትቀመጡባታላችሁም።
“አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳቸው ዘንድ የምትሄድባቸውን አሕዛብ በፊትህ ባጠፋ ጊዜ፥ አንተም በወረስሃቸው ጊዜ፥ በምድራቸውም በተቀመጥህ ጊዜ፥ ከፊትህ ከጠፉ በኋላ እነርሱን ለመከተል እንዳትሻ፥
“አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በተቀመጥህባትም ጊዜ፦ በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ በላዬ አለቃ እሾማለሁ ብትል፥
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህች ናት፤ እነሆም፥ በዐይንህ እንድታያት አደረግሁህ፤ ነገር ግን ወደዚያች አትገባም” አለው።
እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰማርያቸው ጋር ነበሩ፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ እንዲሁ ነበሩ። [ኢያሱም በየድንበሮቻቸው ምድርን ማካፈልን ጨረሰ። የእስራኤል ልጆችም ለኢያሱ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ድርሻውን ሰጡት፤ እርሱ የሚፈልጋትን ከተማ በኤፍሬም ተራራ የምትገኘውን ቴምናሴራን ሰጡት፤ ከተማም ሠራባት፤ በውስጧም ተቀመጠ። ኢያሱም በምደረ በዳ በመንገድ የተወለዱትን የገረዘባቸውን የድንጋይ ባልጩቶች ወስዶ በቴምናሴራ አኖራቸው።]
አምላክህ ኮሞስ የሚሰጥህን የምትወርስ አይደለህምን? እኛም አምላካችን እግዚአብሔር ከፊታችን ያስወጣቸውን የእነርሱን ምድር የምንወርስ አይደለንምን?
ያዕቆብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብጻውያን አስጨነቁአቸው፤ አባቶቻችሁም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን ላከ፤ አባቶቻችሁንም ከግብጽ አውጥተው በዚህ ቦታ አኖሩአቸው።