አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
ኤርምያስ 6:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም ሀገር ቀረፋን ታቀርቡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፤ ቍርባናችሁም ደስ አያሰኘኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕጣን ከሳባ ምድር፣ ጣፋጩ ከሙን ከሩቅ አገር ቢመጣ ምን ይጠቅመኛል? የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን አልቀበልም፤ ሌላውም መሥዋዕታችሁ ደስ አያሰኙኝም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም አገር የከበረውንም ዘይት ታመጡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፥ ሌላ መሥዋዕታችሁም ደስ አያሰኘኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሳባ የሚያመጡልኝ ዕጣን፥ ከሩቅ አገሮች የሚያመጡልኝ ቅመማቅመም ሁሉ ለእኔ ምን ይረባኛል? መባቸውን አልቀበለውም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም አገር ቀረፋን ታቀርቡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም ሌላ መሥዋዕታችሁም ደስ አያሰኘኝም። |
አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቶ፥ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቶ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር።
ከንቱን የሚናገር ይግባና ይይ፤ ልቡ በላዩ ላይ ኀጢአትን ሰበሰበ፤ ወደ ሜዳ ይወጣል ይናገራልም፥ በእኔም ላይ ይተባበራል።
“አንተም ክቡሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተመረጠ የከርቤ አበባ አምስት መቶ ሰቅል፥ የዚህም ግማሽ ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ ያማረ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤
“የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምንድን ነው?” ይላል እግዚአብሔር፤ “የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ ጠግቤአለሁ፤ የበሬና የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘኝም።
የግመሎች መንጋ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የምድያምና የኤፋ ግመሎች ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ወርቅንና ዕጣንን ይዘው ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ማዳን ያበሥራሉ።
በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።
እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፥ “መቅበዝበዝን ወድደዋል፤ እግራቸውንም አልከለከሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አይለውም፤ በደላቸውንም አሁን ያስባል፤ ኀጢአታቸውንም ይጐበኛል።”
ቢጾሙ ጸሎታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ቢያቀርቡም ደስ አልሰኝባቸውም፤ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ።”
እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁላችሁ ኀጢአታችሁን ተዉ፤ ከዚህ በኋላ ስሙኝ፤ ቅዱሱን ስሜንም ከእንግዲህ ወዲህ በኀጢአታችሁና በመባችሁ አታርክሱ።
የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች እነዚህ ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ንግድሽን በጥሩ ሽቱና በከበረ ድንጋይ ሁሉ፥ በወርቅም አደረጉ።
መሥዋዕትንም ቢሠዉ፥ ሥጋንም ቢበሉ፤ እግዚአብሔር አይቀበላቸውም፤ አሁንም በደላቸውን ያስባል፤ በኀጢአታቸውም ይበቀላቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብፅ ይመለሳሉ፤ በአሦርም ርኩስ ነገርን ይበላሉ።
ለእግዚአብሔርም የወይን ጠጅን ቍርባን አያቀርቡም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤ እንደ ኀዘንም እንጀራ ይሆንባቸዋል፤ የሚበላውም ሁሉ ይረክሳል፤ እንጀራቸውም ለሰውነታቸው ይሆናል እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይገባም።
በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።