መዝሙር 66 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት መዝሙር። 1 እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ እኛም በሕይወት እንኑር 2 መንገድህን በምድር፥ በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ ማዳንህን እናውቅ ዘንድ፥ 3 አቤቱ፥ አሕዛብ ያመሰግኑሃል፥ አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑሃል። አሕዛብ ደስ ይላቸዋል፥ ሐሤትም ያደርጋሉ። 4 ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥ አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና 5 አቤቱ፥ አሕዛብ ያመሰግኑሃል። አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑሃል። 6 ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤ እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል፥ የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል። 7 እግዚአብሔር ይባርከናል፥ የምድርም ዳርቻዎች ሁሉ ይፈሩታል። |