Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 30:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “አን​ተም ክቡ​ሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተ​መ​ረጠ የከ​ርቤ አበባ አም​ስት መቶ ሰቅል፥ የዚ​ህም ግማሽ ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ ያማረ የጠጅ ሣርም እን​ዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ምርጥ ቅመሞችን፣ ዐምስት መቶ ሰቅል ፈሳሽ ከርቤ፣ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጣፋጭ ቀረፋ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ከሙን፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 “ምርጥ የሆኑትን ቅመሞች ለራስህ ውሰድ፤ ፈሳሽ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል የቀረፋ ቅመም፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ምርጥ የሆኑ ቅመሞችን፥ ስድስት ኪሎ ግራም ፈሳሽ ከርቤ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን ቀረፋ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን የጠጅ ሣርና፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አንተም ክቡሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተመረጠ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽም ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 30:23
20 Referencias Cruzadas  

ዳንና ያዋን፤ ከኦ​ሴል የተ​ሠራ ብረ​ት​ንና ብር​ጕ​ድን፥ ቀረ​ፋ​ንም ያመ​ጡ​ልሽ ነበር።


ናር​ዶስ ከቀጋ ጋር፥ የሽቱ ሣርና ቀረ​ፋም፥ ከሊ​ባ​ኖስ እን​ጨ​ቶች ጋር፥ ከር​ቤና እሬት ከክ​ቡር ሽቱ ሁሉ ጋር።


የሳ​ባና የራ​ዕማ ነጋ​ዴ​ዎች እነ​ዚህ ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ንግ​ድ​ሽን በጥሩ ሽቱና በከ​በረ ድን​ጋይ ሁሉ፥ በወ​ር​ቅም አደ​ረጉ።


ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣ​ንን፥ ከሩ​ቅም ሀገር ቀረ​ፋን ታቀ​ር​ቡ​ል​ኛ​ላ​ችሁ? የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አል​ቀ​በ​ለ​ውም፤ ቍር​ባ​ና​ች​ሁም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።


ውዴ ለእኔ በጡ​ቶች መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ያ​ርፍ እንደ ተቋ​ጠረ ከርቤ ነው።


የሽ​ቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ሽቱ ነው፤ ስለ​ዚህ ደና​ግል ወደ​ዱህ።


በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ፥ በም​ድር ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት እን​ድ​ታዩ ኑ።


የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የቅ​ብ​ዐ​ቱን ዘይት፥ ጥሩ​ው​ንም የጣ​ፋጭ ሽቱ ዕጣን በቀ​ማሚ ብል​ሃት እንደ ተሠራ አደ​ረገ።


የመ​ብ​ራ​ትም ዘይት፥ ለቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትና ለጣ​ፋጭ ዕጣን ቅመም፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ብር​ጉ​ድም አም​ስት መቶ ሰቅል እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የወ​ይራ ዘይ​ትም አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


የሚ​ቀ​ቡ​ትን የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ለመ​ቅ​ደሱ የሚ​ያ​ጥ​ኑ​ትን ዕጣን እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ ሁሉ ያድ​ርጉ።”


ለመ​ብ​ራ​ትም፥ ለቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትም፥ ለጣ​ፋጭ ዕጣ​ንም ሽቱ​ንና ዘይ​ትን አመጡ።


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈ​ሰ​ሰው፤ ሳመ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በር​ስቱ ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምል​ክቱ ይህ ነው።


ካህ​ኑም ሳዶቅ ከድ​ን​ኳኑ የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎ​ሞ​ንን ቀባ፤ መለ​ከ​ትም ነፋ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ሰሎ​ሞን ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” አሉ።


ከካ​ህ​ና​ቱም ልጆች አን​ዳ​ን​ዶቹ ዕጣ​ኑ​ንና የሽ​ቱ​ውን ቅባት ያዘ​ጋጁ ነበር።


ዕጣ​ንም በገ​ን​ዘብ አል​ገ​ዛ​ህ​ል​ኝም፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ት​ህ​ንም ስብ አል​ተ​መ​ኘ​ሁም፤ ነገር ግን በኀ​ጢ​አ​ት​ህና በበ​ደ​ልህ በፊቴ ቁመ​ሃል።


የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር በመ​ብ​ራቱ ዘይት በጣ​ፋ​ጩም ዕጣን ላይ ፥ ሁል​ጊ​ዜም በሚ​ቀ​ር​በው በእ​ህሉ ቍር​ባ​ንና በቅ​ባቱ ዘይት ላይ ሹም ነው፤ ድን​ኳ​ኑን ሁሉ፥ በእ​ር​ሱም ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ፥ መቅ​ደ​ሱ​ንና ዕቃ​ውን ይጠ​ብ​ቃል።”


ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶቹ በአ​ገ​ል​ግ​ሎቱ ዕቃ​ዎች በመ​ቅ​ደሱ ዕቃ ሁሉ፥ በመ​ል​ካ​ሙም ዱቄት፥ በወ​ይን ጠጁም፥ በዘ​ይ​ቱም፥ በዕ​ጣ​ኑም፥ በሽ​ቱ​ውም ላይ ሹሞች ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios