ኤርምያስ 50:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍሬዋን ሁሉ አድርቁባት፤ ወደ መታረድም ይውረዱ፤ ቀናቸው ደርሳለችና፥ እነሱን የሚበቀሉበት ጊዜ ደርሷልና ወዮላቸው! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይፈኖቿን ሁሉ ዕረዱ፤ ወደ መታረጃም ይውረዱ! የሚቀጡበት ጊዜ፣ ቀናቸው ደርሷልና ወዮላቸው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ፥ ወደ መታረድም ይውረዱ፤ ቀናቸው፥ የመጐብኘታቸው ጊዜ ደርሶአልና ወዮላቸው! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወታደሮቻቸውን፥ ወደ ማረጃ ቦታ ወርደው እንደሚታረዱ የዕርድ ኰርማዎች ወስዳችሁ ግደሉ፤ የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ ለባቢሎን ሕዝብ ወዮላቸው! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ፥ ወደ መታረድም ይውረዱ፥ ቀናቸው፥ የመጐብኘታቸው ጊዜ፥ ደርሶአልና ወዮላቸው! |
እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፤ በበግ ስብ፥ በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ስብ ወፍራለች።
ኀያላን ከእነርሱ ጋር፥ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፤ ምድራቸውም በደም ትሰክራለች፤ በስባቸውም ትወፍራለች።
አንተ ግን አቤቱ! ዐውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፤ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፤ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፤ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።
ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደ የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች! አልቅሱ፤ እናንተም የበጎች አውራዎች! ጩኹ።
የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገዛሉ፤ በዚያን ጊዜም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ለእርሱ ይገዙለታል።
በእርስዋም ያሉ የተቀጠሩ ሠራተኞች በእርስዋ ተቀልበው እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የጥፋታቸው ቀንና የቅጣታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፤ በአንድነትም ሸሹ፤ አልቆሙምም።
ሞዓብ ፈርሳለች፤ ከተሞቹዋም ጠፍተዋል፤ የተመረጡትም ጐልማሶችዋ ወደ መታረድ ወርደዋል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እርስዋን በምጐበኝበት ዓመት በሞአብ ላይ ይህን አመጣለሁ፤ በፍርሀት የሸሸ በጕድጓድ ውስጥ ይወድቃል፤ ከጕድጓድም የወጣ በወጥመድ ይያዛል፤ ይላል እግዚአብሔር።
“ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም በሬዎች ቷጋላችሁና፤
ትዕቢተኛ ሆይ! አንቺን የሚበቀሉበት ጊዜ፥ ቀንሽ ደርሶአልና እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሣን። እኔ እንደማለቅስ ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝ የለም፤ ጠላቶች ሁሉ መከራዬን ሰምተዋል፤ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፤ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቃል ታመጣለህ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።
ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና፤” እያሉ ይናገራሉ።
አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፤ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ “መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።