ያዕቆብም ከሁለቱ ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሰቂሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።
ኤርምያስ 41:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውንም ቀድደው እያለቀሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው የያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ፥ ከሰማርያም መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰማንያ ሰዎች ጢማቸውን ተላጭተው፣ ልብሳቸውን ቀድደው፣ ገላቸውን ነጭተው የእህል ቍርባንና ዕጣን በመያዝ ከሴኬም፣ ከሴሎና ከሰማርያ ወደ እግዚአብሔር ቤት ለማቅረብ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጢማቸውን ላጭተው ልብሳቸውንም ቀድደው ገላቸውንም ተልትለው፥ በጌታ ቤት ለማቅረብ የእህል ቁርባንና ዕጣን በእጃቸው ይዘው፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ ከሰማርያም መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሴኬም፥ ከሴሎና ከሰማርያ ሰማኒያ ሰዎች በድንገት መጡ፤ እነርሱም በሐዘን ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውን ቀደው፥ ፊታቸውን ነጭተው ነበር፤ ለቤተ መቅደስም መባ የሚያቀርቡትን እህልና ዕጣን ይዘው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጢማቸውን ላጭተው ልብሳቸውንም ቀድደው ገላቸውንም ነጭተው፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው እየያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ ከሰማርያም መጡ። |
ያዕቆብም ከሁለቱ ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሰቂሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።
ሐኖንም የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ የጢማቸውን ገሚስ ላጨ፤ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ከሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።
ዘንበሪም ከዚያች ተራራ ባለቤት ከሴሜር በሁለት መክሊት ብር የሳምሮንን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ከተማ ሠራ፤ የሠራትንም ከተማ በተራራው ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራት።
በይሁዳም ንጉሥ በኢዮሳፍጥ በሁለተኛው ዓመት የዘንበሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ በሰማርያ ሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ።
የንጉሡም የአበዛዎች አለቃ የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ። የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ።
ሐናንም የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ የጢማቸውን ግማሽ አስላጫቸው፤ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ለሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።
ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል።
ታላላቆችና ታናናሾች በዚች ምድር ይሞታሉ ፥ አይቀበሩም ሰዎችም አያለቅሱላቸውም፤ ስለ እነርሱም ፊት አይነጩላቸውም፤ ራስንም አይላጩላቸውም፤
በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃነት አለ፤ ጽሕማቸውን ሁሉ ይላጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፤ ሁሉም በወገባቸው ማቅን ይታጠቃሉ።
“ነገር ግን በቀድሞ ዘመን ስሜን ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደ ነበረው ስፍራዬ ሂዱ፤ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ያደረግሁበትን እዩ።
ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግሁ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት፥ እናንተም በምትተማመኑበት ቤት ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ እንዲሁ አደርጋለሁ።
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፥ ቍጣው የዘገየ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።”
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፤ በዚያም የምስክሩን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው።
የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አፅም ያዕቆብ በሰቂማ ከሚኖሩ ከአሞራውያን በመቶ በጎች በገዛው ለዮሴፍ ድርሻ አድርጎ በሰጠው እርሻ በአንዱ ክፍል በሰቂማ ቀበሩት።
የይሩበኣል ልጅ አቤሜሌክም ወደ ሰቂማ ወደ እናቱ ወንድሞች ሄደ፤ ለእነርሱም፥ ለእናቱ አባት ቤተ ሰቦችም ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፦
በየዓመቱም ወደ እግዚአብሔር ቤት በሚወጣበት ጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር፤ እርስዋም ትበሳጭና ታለቅስ ነበር። እህልም አትበላም ነበር።