Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 12:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ወደ ሰቂማ መጥ​ተው ነበ​ርና ሮብ​ዓም ወደ ሰቂማ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እስራኤላውያን ሁሉ ሊያነግሡት ወደ ሴኬም መጥተው ስለ ነበር፣ ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ፤ በዚያም እርሱን ለማንገሥ የፈለጉ በእስራኤል ሰሜናዊ ግዛት የሚኖሩ እስራኤላውያን ተሰብስበው ይጠብቁት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ፤ በዚያም እርሱን ለማንገሥ የፈለጉ በእስራኤል ሰሜናዊ ግዛት የሚኖሩ እስራኤላውያን ተሰብስበው ይጠብቁት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እስራኤል ሁሉ ያነግሡት ዘንድ ወደ ሴኬም መጥተው ነበርና ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 12:1
14 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚ​ያች ምድር አለፈ፤ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በዚ​ያን ጊዜ በዚ​ያች ምድር ነበሩ።


ሰሎ​ሞ​ንም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም ሮብ​ዓም በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሰቂ​ማን ሠርቶ በዚያ ተቀ​መጠ፤ ደግ​ሞም ከዚያ ወጥቶ ፋኑ​ኤ​ልን ሠራ።


ሮብ​ዓ​ምም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመጣ ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ልን ወግ​ተው መን​ግ​ሥ​ቱን ወደ ሮብ​ዓም ይመ​ልሱ ዘንድ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ቤት የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አንድ መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞች ጐል​ማ​ሶ​ችን ሰበ​ሰበ።


ለን​ጉሥ ከቀን በላይ ቀንን ትጨ​ም​ራ​ለህ፥ ዓመ​ታ​ቱም ከት​ው​ልድ ወደ ትው​ልድ ይሆ​ናሉ።


ጢማ​ቸ​ውን ላጭ​ተው፥ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ቀድ​ደው እያ​ለ​ቀሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያቀ​ርቡ ዘንድ የእ​ህል ቍር​ባ​ንና ዕጣን በእ​ጃ​ቸው የያዙ፥ ሰማ​ንያ ሰዎች ከሴ​ኬ​ምና ከሴሎ፥ ከሰ​ማ​ር​ያም መጡ።


ወደ ሴኬ​ምም አፍ​ል​ሰው አብ​ር​ሃም ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በገ​ን​ዘቡ በገ​ዛው መቃ​ብር ቀበ​ሩ​ዋ​ቸው።


በን​ፍ​ታ​ሌም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በገ​ሊላ ቃዴ​ስን፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሴኬ​ምን፥ በይ​ሁ​ዳም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ኬብ​ሮን የም​ት​ባ​ለ​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ለዩ።


ኢያ​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴሎ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጠራ​ቸው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አቆ​ማ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከግ​ብፅ ያወ​ጡ​ትን የዮ​ሴ​ፍን አፅም ያዕ​ቆብ በሰ​ቂማ ከሚ​ኖሩ ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን በመቶ በጎች በገ​ዛው ለዮ​ሴፍ ድርሻ አድ​ርጎ በሰ​ጠው እርሻ በአ​ንዱ ክፍል በሰ​ቂማ ቀበ​ሩት።


የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ወደ ሰቂማ ወደ እናቱ ወን​ድ​ሞች ሄደ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም፥ ለእ​ናቱ አባት ቤተ ሰቦ​ችም ሁሉ እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፦


የሰ​ቂ​ማም ሰዎች ሁሉ፥ የመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት ሁሉ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሄደ​ውም በሰ​ቂማ በዐ​ምዱ አጠ​ገብ ባለው የወ​ይራ ዛፍ በታች አቤ​ሜ​ሌ​ክን አነ​ገሡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos