ተራሮችን ተመለከትሁ፤ እነሆም ይንቀጠቀጡ ነበር፤ ኮረብቶችም ሁሉ ይናወጡ ነበር።
ተራሮችን ተመለከትሁ፣ እነሆ ይንቀጠቀጡ ነበር፤ ኰረብቶችም ሁሉ ተናጡ።
ተራሮችን አየሁ፥ እነሆም፥ ተንቀጠቀጡ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ።
ተራራዎችን ተመለከትኩ፤ እነርሱም በመንቀጥቀጥ ላይ ናቸው፤ ኰረብቶችንም አየሁ፤ እነሆ ወዲያና ወዲህ በመናጥ ላይ ናቸው።
እርሱም አለ፥ “ነገ ውጣ፤ በተራራውም ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቁም። እነሆም፥ እግዚአብሔር በዚያ አለፈ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ፤ ዓለቶቹንም ሰባበረ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ የምድር መናወጥ ሆነ፤ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም።
የእግዚአብሔር ሕግ ንጹሕ ነው፤ ነፍስንም ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትንም ጠቢባን ያደርጋል።
ለነፍሳቸው መብልን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርን በልባቸው ፈተኑት።
በምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ አመስግኑ፥ ደስም ይበላችሁ፥ ዘምሩም።
እግዚአብሔርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጽመው ደነገጡ።
ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት በጽኑ ቍጣው ቀንም ሰማያት ይንቀጠቀጣሉ፤ ምድርም ከመሠረቷ ትናወጣለች።
ምድር በወይን እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች፤ ሕግን መተላለፍዋም ይከብድባታል፤ ትወድቅማለች፤ ደግማም አትነሣም።
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁንም በላያቸው ዘርግቶ መትቶአቸዋል፤ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፤ ሬሳቸውም በመንገድ መካከል እንደ ጕድፍ ሆኖአል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።
የፈረሶቹን የሩጫ ድምፅ ከዳን ሰማን፤ ከሠራዊቱ ፈረሶች ሩጫ ድምፅ የተነሣም ምድር በመላዋ ተንቀጠቀጠች፤ መጥተውም ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማዪቱንና የተቀመጡባትንም በሉ።
በተራሮቹ ላይ አልቅሱ፤ በምድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍትዋልና፤ የሚመላለስም የለምና ሙሾውንም አሙሹ፤ የሰማይ ወፍ ድምፅንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይሰሙም፤ ደንግጠውም ተማርከው ሄዱ።
ከእግዚአብሔርም ፊት የተነሣ የባሕር ዓሣዎችና የሰማይ ወፎች፥ የምድረ በዳም አራዊት፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፤ ተራሮችም ይገለባበጣሉ፤ ገዳላገደሎችም ይወድቃሉ፤ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።
ተራሮችም በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፥ በገደልም ወርዶ እንደሚፈስስ ውኃ፥ በበታቹ ይቀልጣሉ፥ ሸለቆችም ይሰነጠቃሉ።
ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ፣ የውኃ ሞገድ አልፎአል፣ ቀላዩም ድምፁን ሰጥቶአል፥ እጁንም ወደ ላይ አንሥቶአል።
ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።
ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፤ ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወሰዱ።