Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 24:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ምድር በወ​ይን እንደ ሰከረ ሰው ትን​ገ​ዳ​ገ​ዳ​ለች፤ እንደ ዳስም ትወ​ዛ​ወ​ዛ​ለች፤ ሕግን መተ​ላ​ለ​ፍ​ዋም ይከ​ብ​ድ​ባ​ታል፤ ትወ​ድ​ቅ​ማ​ለች፤ ደግ​ማም አት​ነ​ሣም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ምድር እንደ ሰካራም ዞረባት፤ ነፋስ እንደሚወዘውዘውም ጐጆ ሆነች፣ የዐመፅዋ ሸክም ከባድ ስለ ሆነ ትወድቃለች፤ እንደ ገናም አትነሣም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ምድር እንደ ሰካራም ትንገዳገዳለች፥ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች፤ መተላለፍዋ ከብዷታል፥ ትወድቃለች፥ ደግማም አትነሣም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ምድር እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ በዐውሎ ነፋስ እንደ ተገፋ ጎጆም ትናወጣለች፤ እርስዋም የኃጢአትዋ ሸክም ስለሚጫናት ትወድቃለች፤ መነሣትም አትችልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ምድር እንደ ሰካር ሰው ትንገዳገዳለች፥ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች፥ መተላለፍዋ ይከብድባታል፥ ትወድቅማለች ደግማም አትነሣም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 24:20
26 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ስት መን​ፈ​ስን ልኮ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤ ሰካ​ርም፥ ደም ያዞ​ረ​ውም እን​ዲ​ስት እን​ዲሁ ግብ​ፃ​ው​ያን በሥ​ራ​ቸው ሁሉ ሳቱ።


ዳን ሆይ፥ ሕያው አም​ላ​ክ​ህን! ደግ​ሞም፦ ሕያው የቤ​ር​ሳ​ቤ​ህን አም​ላክ ብለው በሰ​ማ​ርያ መማ​ፀኛ የሚ​ምሉ፥ እነ​ርሱ ይወ​ድ​ቃሉ፥ ደግ​ሞም አይ​ነ​ሡም።”


ደከሙ፤ ደነ​ገ​ጡም፤ ሰከ​ሩም፤ በወ​ይን አይ​ይ​ደ​ለም፤ በጠ​ጅም አይ​ደ​ለም።


አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።


ኖን። በእጄ ስለ​ተ​ታቱ ኀጢ​አ​ቶች ተጋ፤ በአ​ን​ገቴ ላይ ወጥ​ተ​ዋል፤ ጕል​በቴ ደከመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቋ​ቋ​መው በማ​ል​ች​ለው መከራ እጅ ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና።


አን​ተም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ከም​ሰ​ድ​ደው ሰይፍ የተ​ነሣ ጠጡ፤ ስከ​ሩም፤ ተፍ​ገ​ም​ገሙ፤ ውደ​ቁም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ነ​ሡም በላ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የወ​ደቀ አይ​ነ​ሣ​ምን? የሳ​ተስ አይ​መ​ለ​ስ​ምን?


በመ​ጀ​መ​ሪያ አባ​ቶ​ችህ፥ ቀጥ​ሎም አለ​ቆ​ችህ በድ​ለ​ው​ኛል።


የቀ​ረ​ው​ንም ኑሬ​ዬን አጣሁ። ከእ​ኔም ወጣች፥ ተለ​የ​ችም። ድን​ኳ​ኑን ተክሎ እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ርና እን​ደ​ሚ​ሄድ፥ ሊቈ​ረጥ እንደ ተቃ​ረበ ሸማም እን​ዲሁ ነፍሴ በላዬ ሆነች።


በደ​ለ​ኞ​ችና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ግን በአ​ን​ድ​ነት ይቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ተ​ዉት ሁሉ ይጠ​ፋሉ።


የጽ​ዮ​ንም ሴት ልጅ በወ​ይን ቦታ እን​ዳለ ዳስ፥ እንደ አዝ​መራ ጠባ​ቂም ጎጆ፥ እንደ ተከ​በ​በ​ችም ከተማ ሆና ቀረች።


“አቤቱ፥ ፍጻ​ሜ​ዬን አስ​ታ​ው​ቀኝ” አልሁ፥ የዘ​መኔ ቍጥ​ሮች ምን ያህል ናቸው? ዐውቅ ዘን​ድስ ለምን ወደ ኋላ እላ​ለሁ?


ብር​ሃ​ንም ሳይ​ኖር በጨ​ለማ ይር​መ​ሰ​መ​ሳሉ፤ እንደ ሰካ​ራ​ምም ይፍ​ገ​መ​ገ​ማሉ።


እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለ​ምን ያጠ​ፋ​ታል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ጋ​ታል፤ ይገ​ለ​ብ​ጣ​ት​ማል፤ በእ​ር​ስ​ዋም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ይበ​ት​ናል።


እነ​ዚ​ህም ደግሞ ከወ​ይን ጠጅ የተ​ነሣ ይስ​ታሉ፤ ከሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ የተ​ነሣ አላ​ዋ​ቆች ይሆ​ናሉ፤ ካህ​ኑና ነቢዩ ከሚ​ያ​ሰ​ክር መጠጥ የተ​ነሣ ይስ​ታሉ፤ በወ​ይን ጠጅም ይዋ​ጣሉ፤ ከሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ የተ​ነሣ ይበ​ድ​ላሉ፤ ይህም የዐ​ይን ምት​ሐት ነው፤ በፍ​ርድ ይሰ​ና​ከ​ላሉ።


ወጥ​ተ​ውም በእኔ ያመ​ፁ​ብ​ኝን ሰዎች ሬሳ​ቸ​ውን ያያሉ፤ ትላ​ቸው አይ​ሞ​ትም፤ እሳ​ታ​ቸ​ውም አይ​ጠ​ፋም፤ ለሥጋ ለባ​ሽም ሁሉ ምሳሌ ይሆ​ናሉ።”


ተራሮችም ከእርሱ የተነሣ ታወኩ፥ ኮረብቶችም ቀለጡ፣ ምድርና ዓለም የሚኖሩበትም ሁሉ ከፊቱ ተናወጡ።


በኋ​ላም ከሚ​ሆ​ነው ከዚያ ራብ የተ​ነሣ በም​ድር የሆ​ነው ጥጋብ አይ​ታ​ወ​ቅም፤ እጅግ ጽኑ ይሆ​ና​ልና።


ተራ​ሮ​ችን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ይን​ቀ​ጠ​ቀጡ ነበር፤ ኮረ​ብ​ቶ​ችም ሁሉ ይና​ወጡ ነበር።


ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት የባ​ቢ​ሎ​ንን ምድር ባድማ ያደ​ር​ጋት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐሳብ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጸን​ቶ​አ​ልና ምድር ተና​ወ​ጠች፤ ታመ​መ​ችም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios