Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 77 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የአ​ሳፍ ትም​ህ​ርት።

1 ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድ​ምጡ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁ​ንም ወደ አፌ ቃል አዘ​ን​ብሉ።

2 አፌን በም​ሳሌ እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ከቀ​ድሞ ጀምሮ ያለ​ው​ንም ምሳሌ እና​ገ​ራ​ለሁ።

3 የሰ​ማ​ነ​ው​ንና ያየ​ነ​ውን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የነ​ገ​ሩ​ንን፥ ለሚ​መጣ ትው​ልድ ከል​ጆ​ቻ​ቸው አል​ሰ​ወ​ሩም።

4 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ተና​ገሩ፥ ኀይ​ሉ​ንና ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት።

5 ለያ​ዕ​ቆብ ያቆ​መ​ውን ምስ​ክር፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የሠ​ራ​ውን ሕግ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ያዘ​ዘ​ውን ለል​ጆ​ቻ​ቸው ይነ​ግሩ ዘንድ፥

6 የሚ​መጣ ትው​ልድ የሚ​ወ​ለ​ዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነ​ሥ​ተ​ውም ለል​ጆ​ቻ​ቸው ይነ​ግ​ራሉ።

7 ተስ​ፋ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥራ እን​ዳ​ይ​ረሱ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም እን​ዲ​ፈ​ልጉ፤

8 እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሆኑ፥ ጠማ​ማና የም​ታ​ስ​መ​ርር ትው​ልድ፥ ልብ​ዋን ያላ​ቀ​ናች ትው​ልድ፥ መን​ፈ​ስዋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያል​ታ​መ​ነች።

9 የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ቀስ​ታ​ቸ​ውን ገት​ረው ይወጉ ነበር። በሰ​ልፍ ቀን ወደ ኋላ ተመ​ለሱ።

10 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኪዳን አል​ጠ​በ​ቁ​ምና፥ በሕ​ጉም ለመ​ሄድ እንቢ አሉ፤

11 ረድ​ኤ​ቱ​ንና ያሳ​ያ​ቸ​ውን ተአ​ም​ራ​ቱን ረሱ፥

12 በግ​ብጽ ሀገ​ርና በጣ​ኔ​ዎስ በረሃ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት የሠ​ራ​ውን ተአ​ም​ራት።

13 ባሕ​ርን ከፍሎ አሳ​ለ​ፋ​ቸው፤ ውኆ​ችን እንደ ረዋት ውኃ አቆመ።

14 ቀን በደ​መና መራ​ቸው፥ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ በእ​ሳት ብር​ሃን።

15 ዓለ​ቱን በም​ድረ በዳ ሰነ​ጠቀ፤ ከብዙ ጥልቅ እን​ደ​ሚ​ገኝ ያህል አጠ​ጣ​ቸው።

16 ውኃ​ንም እንደ ወን​ዞች አፈ​ሰሰ። ውኃ​ንም ከዓ​ለት አፈ​ለቀ፥

17 ነገር ግን እር​ሱን መበ​ደ​ልን እን​ደ​ገና ደገሙ፥ ልዑ​ል​ንም በም​ድረ በዳ አስ​መ​ረ​ሩት።

18 ለነ​ፍ​ሳ​ቸው መብ​ልን ይፈ​ልጉ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በል​ባ​ቸው ፈተ​ኑት።

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ ብለው አሙት፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድረ በዳ ማዕ​ድን ያሰ​ናዳ ዘንድ

20 ዓለ​ቱን ይመታ ዘንድ ውኃ​ንም ያፈስ ዘንድ ይች​ላ​ልን? እን​ጀ​ራን መስ​ጠ​ትና ለሕ​ዝ​ቡስ ማዕ​ድን መሥ​ራት ይች​ላ​ልን?”

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ፤ በያ​ዕ​ቆ​ብም ላይ እሳት ነደደ፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ወጣ፤

22 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላ​መ​ኑ​ምና፥ በማ​ዳ​ኑም አል​ተ​ማ​መ​ኑ​ምና።

23 ደመ​ና​ው​ንም ከላይ አዘዘ፥ የሰ​ማ​ይ​ንም ደጆች ከፈተ፤

24 ይበ​ሉም ዘንድ መናን አዘ​ነ​በ​ላ​ቸው፥ የሰ​ማ​ይ​ንም እን​ጀራ ሰጣ​ቸው።

25 የመ​ላ​እ​ክ​ት​ንም እን​ጀራ የሰው ልጆች በሉ። የሚ​በ​ቃ​ቸው ስን​ቅ​ንም ላከ​ላ​ቸው።

26 ከሰ​ማይ ዐዜ​ባዊ ነፋ​ስን አስ​ነሣ፥ በኀ​ይ​ሉም መስ​ዓዊ ነፋ​ስን አመጣ፤

27 ሥጋን እንደ አፈር፥ የሚ​በ​ር​ሩ​ት​ንም ወፎች እንደ ባሕር አሸዋ አዘ​ነ​በ​ላ​ቸው፤

28 በሰ​ፈ​ራ​ቸው መካ​ከል፥ በድ​ን​ኳ​ና​ቸ​ውም ዙሪያ ወደቀ።

29 በሉ፥ እጅ​ግም ጠገቡ፤ ለም​ኞ​ታ​ቸ​ውም ሰጣ​ቸው።

30 ከወ​ደ​ዱ​ትም አላ​ሳ​ጣ​ቸ​ውም፤ መብ​ላ​ቸ​ውም ገና በአ​ፋ​ቸው ሳለ፥

31 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት በላ​ያ​ቸው መጣ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ​ዎ​ቹን ገደለ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ምር​ጦች አሰ​ና​ከለ።

32 ከዚ​ህም ሁሉ ጋር እንደ ገና እር​ሱን በደሉ፥ ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም አላ​መ​ኑም፤

33 ቀኖ​ቻ​ቸ​ውም በከ​ንቱ አለቁ፥ ዓመ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በች​ኮላ አለፉ።

34 በገ​ደ​ላ​ቸ​ውም ጊዜ ወዲ​ያው ፈለ​ጉት፤ ተመ​ለሱ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ገሠ​ገሡ፤

35 ረዳ​ታ​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸ​ውም ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ዐሰቡ።

36 በአ​ፋ​ቸው ብቻ ወደ​ዱት፤ በአ​ን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም ዋሹ​በት፤

37 ልባ​ቸ​ውም ከእ​ርሱ ጋር አል​ቀ​ናም፥ በቃል ኪዳ​ኑም አል​ተ​ማ​መ​ኑ​ትም።

38 እርሱ ግን መሐሪ ነው፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ይቅር አላ​ቸው፥ አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ው​ምም፤ ቍጣ​ው​ንም መመ​ለስ አበዛ፥ መዓ​ቱ​ንም ሁሉ አላ​ቃ​ጠ​ለም።

39 ሥጋም እንደ ሆኑ ዐሰበ። መን​ፈስ ከወጣ በኋላ አይ​መ​ለ​ስም

40 በም​ድረ በዳ ምን ያህል አስ​ቈ​ጡት፥ በበ​ረ​ሃም አሳ​ዘ​ኑት።

41 ተመ​ለሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፈተ​ኑት፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ አሳ​ዘ​ኑት።

42 እነ​ር​ሱም እጁን አላ​ሰ​ቡም፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ያዳ​ነ​በ​ትን፥

43 በግ​ብፅ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራ​ቱን፥ በጣ​ኔ​ዎ​ስም በረሃ ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን።

44 ወን​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወደ ደም ለወጠ፥ ምን​ጮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ደግሞ እን​ዳ​ይ​ጠጡ።

45 ዝን​ቦ​ች​ንም በላ​ያ​ቸው ሰደ​ደ​ባ​ቸው፥ በሉ​አ​ቸ​ውም፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን ሰደደ፥ አረ​ከ​ሳ​ቸ​ውም።

46 ፍሬ​ያ​ቸ​ውን ለኩ​ብ​ኩባ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንም ለአ​ን​በጣ ሰጠ።

47 ወይ​ና​ቸ​ው​ንም በበ​ረዶ፥ በለ​ሳ​ቸ​ው​ንም በው​ርጭ አጠፋ።

48 እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ለበ​ረዶ፥ ሀብ​ታ​ቸ​ው​ንም ለእ​ሳት ሰጠ።

49 የመ​ዓ​ቱን መቅ​ሠ​ፍት በላ​ያ​ቸው ሰደደ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ መዓ​ት​ንም መከ​ራ​ንም በክ​ፉ​ዎች መላ​እ​ክት ሰደደ።

50 ለቍ​ጣው መን​ገ​ድን ጠረገ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ከሞት አላ​ዳ​ና​ትም፥ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሞት ውስጥ ዘጋ፤

51 በኵ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ በግ​ብፅ ምድር፥ የድ​ካ​ማ​ቸ​ው​ንም መጀ​መ​ሪያ በቤ​ቶ​ቻ​ቸው ውስጥ ገደለ።

52 ሕዝ​ቡን ግን እንደ በጎች አሰ​ማ​ራ​ቸው፥ እንደ መን​ጋም ወደ ምድረ በዳ አወ​ጣ​ቸው።

53 በተ​ስ​ፋም መራ​ቸው አል​ፈ​ሩ​ምም፥ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ባሕር ደፈ​ና​ቸው።

54 ወደ መቅ​ደ​ሱም ተራራ ወሰ​ዳ​ቸው፥ ቀኙ ወደ ፈጠ​ረ​ችው ተራራ፤

55 ከፊ​ታ​ቸ​ውም አሕ​ዛ​ብን አባ​ረረ፥ ርስ​ቱ​ንም በገ​መድ አካ​ፈ​ላ​ቸው፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወገ​ኖች በቤ​ታ​ቸው አኖረ።

56 ነገር ግን ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈተ​ኑት፥ አሳ​ዘ​ኑ​ትም፥ ምስ​ክ​ሩ​ንም አል​ጠ​በ​ቁም፤

57 ተመ​ለ​ሱም፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከዱ፤ እንደ ጠማማ ቀስ​ትም ሆኑ፤

58 በኮ​ረ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አስ​ቈ​ጡት፥ በተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አስ​ቀ​ኑት።

59 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ። እስ​ራ​ኤ​ል​ንም እጅግ ናቃ​ቸው፤

60 የሴ​ሎ​ም​ንም ድን​ኳን ተዋት፥ በሰ​ዎች መካ​ከል ያደ​ረ​ባ​ትን ድን​ኳ​ኑን።

61 ኀይ​ላ​ቸ​ውን ለም​ርኮ፥ ጌጣ​ቸ​ው​ንም በጠ​ላት እጅ ሰጠ።

62 ሕዝ​ቡ​ንም በጦር ውስጥ ዘጋ​ቸው፥ ርስ​ቱ​ንም ቸል አላ​ቸው።

63 ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን እሳት በላ​ቻ​ቸው፥ ቈነ​ጃ​ጅ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አላ​ለ​ቀ​ሱም።

64 ካህ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም በሰ​ይፍ ወደቁ፥ ባል​ቴ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አላ​ለ​ቀ​ሱ​ላ​ቸ​ውም።

65 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ን​ቅ​ልፍ እን​ደ​ሚ​ነቃ ተነሣ፥ የወ​ይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኀያ​ልም ሰው፤

66 ጠላ​ቶ​ቹ​ንም በኋ​ላው ገደለ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንም ኀሣር ሰጣ​ቸው።

67 የዮ​ሴ​ፍ​ንም ድን​ኳን ተዋት፥ የኤ​ፍ​ሬ​ም​ንም ወገን አል​መ​ረ​ጠ​ውም፤

68 የይ​ሁ​ዳን ወገን ግን መረጠ፥ የወ​ደ​ደ​ውን የጽ​ዮ​ንን ተራራ።

69 መቅ​ደ​ሱን እንደ አር​አ​ያም ሠራ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም በም​ድር ውስጥ መሠ​ረ​ታት።

70 ባሪ​ያው ዳዊ​ት​ንም መረ​ጠው፥ ከበ​ጎ​ቹም መንጋ ውስጥ ወሰ​ደው፤

71 ከሚ​ያ​ጠቡ በጎ​ችም በኋላ፥ ባሪ​ያ​ውን ያዕ​ቆ​ብን ርስ​ቱን እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ ወሰ​ደው።

72 በልቡ ቅን​ነት ጠበ​ቃ​ቸው፥ በእ​ጁም ጥበብ መራ​ቸው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos