Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እር​ሱም አለ፥ “ነገ ውጣ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁም። እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ አለፈ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ትል​ቅና ብርቱ ነፋስ ተራ​ሮ​ቹን ሰነ​ጠቀ፤ ዓለ​ቶ​ቹ​ንም ሰባ​በረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በነ​ፋሱ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም። ከነ​ፋ​ሱም በኋላ የም​ድር መና​ወጥ ሆነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በም​ድር መና​ወጥ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔርም፣ “እግዚአብሔር በዚያ ያልፋልና ወደ ተራራው ወጥተህ በእግዚአብሔር ፊት ቁም” አለው። ከዚያም ታላቅና ኀይለኛ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጣጠቀ፤ ዐለቶችንም በእግዚአብሔር ፊት ብትንትናቸውን አወጣ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ከነፋሱም ቀጥሎ የምድር መነዋወጥ ሆነ፤ እግዚአብሔር ግን በምድር መነዋወጡ ውስጥ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታም ኤልያስን “ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም” አለው፤ ከዚህ በኋላ ጌታ በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኰረብቶችን ሰነጣጠቀ፤ አለቶችንም ሰባበረ፤ ጌታ ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ ጌታ ግን በምድሪቱ ነውጥ ውስጥ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔርም ኤልያስን “ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም” አለው፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኰረቶችን ሰነጣጠቀ፤ አለቶችንም ሰባበረ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ እግዚአብሔር ግን በምድሪቱ ነውጥ ውስጥ አልነበረም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርሱም “ውጣ፤ በተራራውም ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቁም፤” አለ። እነሆም፥ እግዚአብሔር አለፈ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ፤ ዐለቶቹንም ሰባበረ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ የምድር መናወጥ ሆነ፤ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 19:11
31 Referencias Cruzadas  

ኤል​ዩስ ንግ​ግ​ሩን ካቆመ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​መ​ናና በዐ​ውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮ​ብን ጠየ​ቀው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦


እኔ በደ​ሌን አው​ቃ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ቴም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነውና።


ለወ​ን​ድ​ሞቼ እንደ ባዕድ፥ ለአ​ባ​ቴና ለእ​ና​ቴም ልጆች እንደ እን​ግዳ ሆን​ሁ​ባ​ቸው።


የቤ​ትህ ቅን​ዓት በል​ቶ​ኛ​ልና፥ የሚ​ሰ​ድ​ቡ​ህም ስድብ በላዬ ወድ​ቆ​አ​ልና።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን በማ​ለዳ ጊዜ ነጐ​ድ​ጓ​ድና መብ​ረቅ፥ ከባ​ድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅ​ግም የበ​ረታ የቀ​ንደ መለ​ከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰ​ፈ​ሩም የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሲና ተራራ ላይ ወደ ተራ​ራው ራስ ወረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ወደ ተራ​ራው ራስ ጠራው፤ ሙሴም ወጣ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ነጐ​ድ​ጓ​ዱ​ንና መብ​ረ​ቁን፥ የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ፥ ተራ​ራ​ው​ንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው ርቀው ቆሙ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ በዚ​ያም ሁን፤ እኔ የጻ​ፍ​ሁ​ትን ሕግና ትእ​ዛዝ፥ የድ​ን​ጋ​ይም ጽላት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ሕግ​ንም ትሠ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።


ሙሴም ወደ ደመ​ናው ውስጥ ገባ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ወጣ፤ ሙሴም በተ​ራ​ራው ላይ አርባ ቀን፥ አርባ ሌሊ​ትም ቈየ።


ለጥ​ዋ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀህ ሁን፤ ወደ ሲና ተራራ ወጥ​ተህ በዚያ በተ​ራ​ራው ራስ ላይ በፊቴ ቁም።


ጌታም በፊቱ አለፈ፥ “ስሜም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ መሓሪ፥ ይቅር ባይ፥ ከመ​ዓት የራቀ ምሕ​ረቱ የበዛ ጻድቅ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የድ​ም​ፁን ክብር ያሰ​ማል፤ የክ​ን​ዱ​ንም መፈ​ራት፥ በጽኑ ቍጣና በም​ት​በላ እሳት፥ በወ​ጀ​ብም፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም፥ በበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ ይገ​ል​ጣል።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከሰ​ሜን በኩል ዐውሎ ነፋ​ስና ታላቅ ደመና፥ የሚ​በ​ር​ቅም እሳት መጣ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ልም በእ​ሳቱ ውስጥ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ ነገር ነበረ።


እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም ትን​ቢት ተና​ገ​ርሁ፤ ስና​ገ​ርም ድምፅ ሆነ፤ እነ​ሆም መና​ወጥ ሆነ፤ አጥ​ን​ቶ​ች​ንም እየ​ራሱ በሆነ በሰ​ው​ነቱ ከአ​ጥ​ን​ቶች ጋር አንድ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


እግዚአብሔር ትዕግሥተኛ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፣ እግዚአብሔር በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።


የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳልና በተራሮች ሸለቆ ትሸሻላችሁ፣ በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከሆነው ከምድር መናወጥ ፊት እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ፣ አምላኬ እግዚአብሔርም ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል።


መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤


እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ።


ያን​ጊዜ ቃል ምድ​ርን አና​ወ​ጣት፤ “አሁ​ንም እኔ ምድ​ርን እንደ ገና አንድ ጊዜ አና​ው​ጣ​ታ​ለሁ” ብሎ ተና​ገረ፤ ምድ​ርን ብቻም አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ይ​ንም ጭምር እንጂ።


በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።


መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፤ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ።


ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


በሰ​ፈ​ሩና በእ​ር​ሻ​ውም ድን​ጋጤ ሆነ፤ በሰ​ፈሩ የተ​ቀ​መጡ ሕዝ​ብና የሚ​ዋ​ጉ​ትም ሁሉ ተሸ​በሩ፤ መዋ​ጋ​ትም አል​ቻ​ሉም፤ ምድ​ሪ​ቱም ተና​ወ​ጠች፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ታላቅ ድን​ጋጤ መጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos