ኤርምያስ 30:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቃቸውም ከእነርሱ ውስጥ ይሾማል፤ ገዢአቸውም ከመካከላቸው ይወጣል፤ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ እኔም እመልሳቸዋለሁ፤ ወደ እኔ ይመለስ ዘንድ ልብ የሰጠው ማን ነው? ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሪያቸው ከራሳቸው ወገን ይሆናል፤ ገዣቸውም ከመካከላቸው ይነሣል፤ ወደ እኔ አቀርበዋለሁ፤ እርሱም ይቀርበኛል፤ አለዚያማ ደፍሮ፣ ወደ እኔ የሚቀርብ ማን ነው?’ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቃቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ይሆናል፥ ገዥአቸውም ከመካከላቸው ይወጣል፤ እኔ አቀርበዋለሁ እርሱም ይቀርበኛል፤ ይህስ ባይሆን ለነፍሱ ዋስትና ሰጥቶ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የራሳቸው ወገን ከመካከላቸው ተነሥቶ መሪአቸው ይሆናል፤ እኔ ራሴ ስለማመጣው እርሱ ወደ እኔ ይቀርባል፤ አለበለዚያማ ማን ደፍሮ ሊቀርብ ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቃቸው ከእነርሱ ውስጥ ይሆናል፥ ገዥአቸውም ከመካከላቸው ይወጣል፥ እኔ አቀርበዋለሁ እርሱም ይቀርባል፥ ይህስ ባይሆን ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል እግዚአብሔር። |
አብርሃምም እንደገና ነገሩን ደገመ፤ እንዲህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ሠላሳው አላጠፋትም” አለው።
አብርሃምም አለው፥ “አቤቱ እንደገና እናገር ዘንድ ፍቀድልኝ፤ ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ዐሥሩ አላጠፋትም” አለው።
መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከሮሃልያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጎዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤
ወንድሜን ሃናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያንም በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
ከኤዶምያስ፥ ከባሶራ የሚመጣ፥ ልብሱም የቀላ፥ የሚመካ ኀይለኛ፥ አለባበሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የምከራከር፥ ስለ ማዳንም የምፈርድ እኔ ነኝ።
በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል።
እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም እንደ አንበሳ ይወጣል፤ ጐልማሶችንም በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?”
እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና እንደ አንበሳ ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም ምድር ይወጣል፤ ጐልማሶቹንም ሁሉ በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቋቋም እረኛ ማን ነው?
“ባሪያዬም ዳዊት በላያቸው ንጉሥ ይሆናል፤ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል፤ በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ፤ ያደርጓትማል።
የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ ለእነርሱም አንድ አለቃ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።
እንደ ቆሬና ከእርሱም ጋር እንደ ተቃወሙት ሰዎች እንዳይሆን፥ ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እንዳይቀርብ፥ እግዚአብሔር በሙሴ ቃል እንደ ተናገረው፥ ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ አደረጋቸው።
ለቆሬም ለማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አላቸው፥ “ነገ እግዚአብሔር የእርሱ የሚሆኑትን፥ ቅዱሳንም የሆኑትን ያያል፥ ያውቃልም፤ የመረጣቸውንም ሰዎች ወደ እርሱ ያቀርባቸዋል።
እግዚአብሔር እርሱን ለእስራኤል ንስሓን፥ የኀጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ ራስም አዳኝም አደረገው፤ በቀኙም አስቀመጠው።
የሚፈርድስ ማነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን ተለይቶ የተነሣው፥ በእግዚአብሔርም ቀኝ የተቀመጠው፥ ደግሞ ስለ እና የሚፈርደው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ከወንድሞችህ መካከል አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን ለአንተ አለቃ ትሾማለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ሌላ ሰው በአንተ ላይ መሾም አትችልም።
ከወንድሞቻቸው እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ፤ ቃሌንም በአፉ አኖራለሁ፤ እንደ አዘዝሁትም ይነግራቸዋል፤
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የመልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።