ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ይሰማ እንደሆነ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደ ሆነ፥ ስለዚህ ለቀረው ቅሬታ ጸልይ።”
ኤርምያስ 23:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆንበታልና የእግዚአብሔር ሸክም ብላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ አትጥሩ፤ የሠራዊትን ጌታ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን የሕያውን አምላክ ቃል ለውጣችኋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእንግዲህ ግን፣ ‘የእግዚአብሔር ሸክም’ ብላችሁ መናገር አይገባችሁም፤ ምክንያቱም ለሰው ሁሉ የገዛ ራሱ ቃል ሸክሙ ስለሚሆን፣ የአምላካችንን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን፣ የሕያው አምላክን ቃል ታጣምማላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆንበታልና ‘የጌታ ሸክም’ ብላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ አትጥሩ፤ የሠራዊትን ጌታ የአምላካችንን የሕያው እግዚአብሔርን ቃላት ለውጣችኋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ሸክም ብላችሁ ከቶ አትናገሩ፤ የእግዚአብሔር ቃል እንዴት ሸክም ሊሆን ይችላል? እናንተ ግን የሠራዊት ጌታ የሕያው እግዚአብሔርን ቃል ታጣምማላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆንበታልና የእግዚአብሔር ሸክም ይሆንበታልና የእግዚአብሔር ሸክም ብላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ አትጥሩ፥ የሠራዊትን ጌታ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን የሕያውን አምላክ ቃል ለውጣችኋልና። |
ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ይሰማ እንደሆነ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደ ሆነ፥ ስለዚህ ለቀረው ቅሬታ ጸልይ።”
አቤቱ አምላኬ፥ ተመልከተኝ ስማኝም፤ ለሞትም እንዳያንቀላፉ ዐይኖቼን አብራቸው። ጠላቶቼም አሸነፍነው እንዳይሉ፥
አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚያደርገውን ያለቀና የተቈረጠ ነገርን ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራታችሁ እንዳይጸናባችሁ እናንተ ደስ አይበላችሁ።
ኢየሩሳሌም ተፈትታለችና፥ ይሁዳም ወድቃለችና፥ አንደበታቸውም ዐመፅን ስለሚናገር ለእግዚአብሔር አልታዘዙም።
እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።
ኖን። ነቢያትሽ ከንቱና ዕብደትን አይተውልሻል፤ ምርኮሽን ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፤ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።
ጌታውም እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፥ ያልዘራሁትን የማጭድ፥ ያልበተንሁትንም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? እንደ ቃልህ እፈርድብሃለሁ።
እንዲህም አሉአቸው፥ “እናንተ ሰዎች፥ ይህን ነገር ለምን ታደርጋላችሁ? እኛስ እንደ እናንተ የምንሞት ሰዎች አይደለንምን? ነገር ግን ይህን ከንቱ ነገር ትታችሁ ሰማይና ምድርን፥ ባሕርንም በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እናስተምራችኋለን።
እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሣውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደተመለሳችሁ ይናገራሉ።
በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ። በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፤ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።
ዳዊትም በአጠገቡ ለቆሙት ሰዎች፦ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድል፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን ለሚያርቅ ሰው በውኑ ይህ ይደረግለታል? የሕያው አምላክን ጭፍሮች የሚገዳደር ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው?” ብሎ ተናገራቸው።
እኔ ባሪያህ አንበሳና ድብ ገደልሁ፤ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል። እንግዲህ እገድለው ዘንድ፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን አስወግድ ዘንድ ዛሬ አልሄድምን? የሕያው አምላክ ጭፍሮችን ይገዳደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምንድን ነው?”