Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 64:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከተ​አ​ም​ራ​ትህ የተ​ነሣ አሕ​ዛብ ይደ​ን​ግ​ጣሉ፥ በም​ድር ዳር​ቻም የሚ​ኖሩ ይፈ​ራሉ፤ በጥ​ዋት ይወ​ጣሉ፥ ማታም ይደ​ሰ​ታሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በገዛ ምላሳቸው ያሰናክላቸዋል፤ ጥፋትንም ያመጣባቸዋል፤ የሚያዩአቸውም ሁሉ በትዝብት ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል። ድንገተኛ ፍላጻም ያቈስላቸዋል፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር ንግግራቸው በራሳቸው ላይ ተመልሶ እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል። የሚያዩአቸው ሁሉ በፍርሃት ከእነርሱ ይሸሻሉ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 64:8
19 Referencias Cruzadas  

የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።


ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።


ከሰ​ወ​ሩ​ብኝ ወጥ​መድ፥ ዐመ​ፃ​ንም ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች እን​ቅ​ፋት ጠብ​ቀኝ።


ጌታ​ውም እን​ዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገ​ል​ጋይ፥ እኔ ያላ​ስ​ቀ​መ​ጥ​ሁ​ትን የም​ወ​ስድ፥ ያል​ዘ​ራ​ሁ​ትን የማ​ጭድ፥ ያል​በ​ተ​ን​ሁ​ት​ንም የም​ሰ​በ​ስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለ​ህን? እንደ ቃልህ እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ።


እነርሱም “ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል፤” አሉት።


የሚያይሽም ሁሉ ከአንቺ ሸሽቶ፦ ነነዌ ባድማ ሆናለች፣ የሚያለቅስላትስ ማን ነው? የሚያጽናናትንስ ከወዴት እፈልጋለሁ? ይላል።


እስ​ራ​ኤል ለአ​ንተ መሳ​ቂያ አል​ሆ​ነ​ምን? ወይስ በሌ​ቦች መካ​ከል ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልን? ስለ እርሱ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ ራስ​ህን ትነ​ቀ​ን​ቃ​ለህ።


ምድ​ራ​ቸ​ውን ለጥ​ፋ​ትና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ማፍ​ዋጫ አድ​ር​ገ​ዋል፤ የሚ​ያ​ል​ፍ​ባት ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ ራሱ​ንም ያነ​ቃ​ን​ቃል።


ጻድ​ቃን ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጉ፤ ልባ​ች​ሁም የቀና ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ተመኩ።


የሚ​ፈ​ር​ድ​ብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህም ይመ​ሰ​ክ​ሩ​ብ​ሃል።


ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና፤” እያሉ ይናገራሉ።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ እር​ሱም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ንን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።


መድ​ኀ​ኒ​ትን ከጽ​ዮን ለእ​ስ​ራ​ኤል ማን ይሰ​ጣል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ዝ​ቡን ምርኮ በመ​ለሰ ጊዜ፥ ያዕ​ቆብ ደስ ይለ​ዋል እስ​ራ​ኤ​ልም ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።


ጠላ​ቶቼ ወደ ኋላ​ቸው በተ​መ​ለሱ ጊዜ፥ ይታ​መሙ፥ ከፊ​ት​ህም ይጥፉ።


በዙ​ሪ​ያ​ቸው የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ከጩ​ኸ​ታ​ቸው የተ​ነሣ፥ “ምድ​ሪቱ እን​ዳ​ት​ው​ጠን” ብለው ሸሹ።


“ኀይ​ልህ ግሩም ነው” ይላሉ፥ ግር​ማ​ህ​ንም ይነ​ጋ​ገ​ራሉ፥ ብር​ታ​ት​ህ​ንም ያስ​ረ​ዳሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios