ነገሩ እንደዚህ አይደለም፤ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፥ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህም ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የማመጣውን ክፉ ነገር ዐይኖችህ አያዩም።” ይህንም ለንጉሡ ነገሩት።
ኤርምያስ 22:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና፥ የተወለደባትንም ሀገር አያይምና ለሚወጣ እጅግ አልቅሱ እንጂ ለሞተ አታልቅሱ፤ አትዘኑለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእንግዲህ ስለማይመለስ፣ የተወለደባትንም ምድር ዳግመኛ ስለማያይ፣ ለተማረከው ንጉሥ አምርራችሁ አልቅሱ እንጂ፣ ቀድሞ ለሞተው አታልቅሱ፤ አትዘኑም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተወለደባትንም አገር ለማየት ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና ለሚሄደው እጅግ አልቅሱ እንጂ ለሞተው አታልቅሱ አትዘኑለትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ስለ ንጉሥ ኢዮስያስ አታልቅሱ፤ በመሞቱም አትዘኑ፤ ነገር ግን የኢዮስያስ ልጅ ሻሉም፤ ዳግመኛ ወደማይመለስበት ቦታ ስለሚወሰድ፥ የትውልድ አገሩንም ዳግመኛ ስለማያይ፥ ለእርሱ ምርር ብላችሁ አልቅሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና፥ የተወለደባትንም አገር አያይምና ለሚወጣ እጅግ አልቅሱ እንጂ ለሞተ አታልቅሱ አትዘኑለትም። |
ነገሩ እንደዚህ አይደለም፤ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፥ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህም ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የማመጣውን ክፉ ነገር ዐይኖችህ አያዩም።” ይህንም ለንጉሡ ነገሩት።
በእርሱም ዘመን የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ ከአሦር ንጉሥ ጋር ሊጋጠም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉሡም ኢዮስያስ ከእርሱ ጋር ሊጋጠም ወጣ፤ ፈርዖንም በተገናኘው ጊዜ በመጊዶ ገደለው።
የግብፅም ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ የይሁዳን ንጉሥ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ ፋንታ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠ፤ ፈርዖን ኒካዑም ወንድሙን ኢዮአክስን ይዞ ወደ ግብፅ ወሰደው። በዚያም ሞተ። 4 ‘ሀ’ ወርቅንና ብርን ለፈርዖን ሰጠ። በዚያን ጊዜም ምድር በፈርዖን ትእዛዝ ብር መገበሯን ጀመረች። 4 ‘ለ’ እያንዳንዱም እንደሚችለው ለፈርዖን ኒካዑ እንዲገብር ከሀገሪቱ ሕዝብ ወርቅንና ብርን ጠየቀ።
ጻድቅ ሰው እንደጠፋ አያችሁ፤ ይህንም በልባችሁ አላሰባችሁም፤ ጻድቃን ሰዎች ይወገዳሉ፤ ጻድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም።
ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የእዝን እንጀራ አይቈርሱላቸውም፤ ስለ አባታቸውና ስለ እናታቸውም የመጽናናት ጽዋ አያጠጡአቸውም።
በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለ ነገሠው፥ ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣውና ስለማይመለሰው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ፥ ስለ ሳሌም እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፥ “ወንድሜ ሆይ፥ ወዮ! ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! እያለ የሚያለቅስለት ለሌለው ለዚያ ሰው ወዮለት!
አንተም፥ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምሰድደው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፤ ስከሩም፤ ተፍገምገሙ፤ ውደቁም፤ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡም በላቸው።
ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።”
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ቍጣዬና መቅሠፍቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እንዲሁ ወደ ግብፅ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈስስባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለጥፋት ለስድብና ለርግማን ትሆናላችሁ፤ ይችንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩአትም።
በዚያ ለመቀመጥ በልባቸው ተስፋ ወደሚያደርጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሱ ዘንድ በግብፅ ለመኖር ከመጡ ከይሁዳ ቅሬታ ወገን የሚያመልጥና የሚቀር፥ ወደዚያም የሚመለስ አይኖርም፤ ከሚያመልጥም በቀር ማንም አይመለስም።”
“የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ የዐይንህን አምሮት በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ፤ አንተም ዋይ አትበል፤ አታልቅስም፤ እንባህንም አታፍስስ።
ጌታችን ኢየሱስም መለስ ብሎ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ሆይ፥ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ እንጂ ለእኔስ አታልቅሱልኝ።