Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 22:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ነገሩ እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ወደ አባ​ቶ​ችህ እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፥ በሰ​ላ​ምም ወደ መቃ​ብ​ርህ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለህ፤ በዚ​ህም ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የማ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ዐይ​ኖ​ችህ አያ​ዩም።” ይህ​ንም ለን​ጉሡ ነገ​ሩት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ፣ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላም ትቀበራለህ፤ በዚህ ቦታ የማመጣውን መከራ ሁሉ ዐይኖችህ አያዩም።’ ” ሰዎቹም መልሷን ይዘው ወደ ንጉሡ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም ላይ የማመጣው ቅጣት አንተ በዐይንህ ሳታየው እስከምትሞትበት ጊዜ ድረስ ተፈጻሚ አይሆንም፤ ስለዚህም አንተ በሰላም እንድትሞት አደርጋለሁ።’” ሰዎቹም ይህን መልእክት ይዘው ወደ ንጉሥ ኢዮስያስ ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም ላይ የማመጣው ቅጣት አንተ በዐይንህ ሳታየው እስከምትሞትበት ጊዜ ድረስ ተፈጻሚ አይሆንም፤ ስለዚህም አንተ በሰላም እንድትሞት አደርጋለሁ።’ ” ሰዎቹም ይህን መልእክት ይዘው ወደ ንጉሥ ኢዮስያስ ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ስለዚህም ደግሞ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህም ስፍራ ላይ የማመጣውን ክፉ ነገር ዐይኖችህ አያዩም።’” ይህንም ለንጉሡ አወሩለት።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 22:20
10 Referencias Cruzadas  

ወደ አባ​ቶ​ች​ህም ትሄድ ዘንድ ዕድ​ሜህ በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ ከአ​ብ​ራ​ክህ የተ​ወ​ለደ ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አጸ​ና​ለሁ።


አብ​ር​ሃ​ምም መል​ካም ሽም​ግ​ል​ናን ሸም​ግሎ፥ ዘመ​ኑ​ንም ፈጽሞ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​መ​ለ​ስ​ምና፥ የተ​ወ​ለ​ደ​ባ​ት​ንም ሀገር አያ​ይ​ምና ለሚ​ወጣ እጅግ አል​ቅሱ እንጂ ለሞተ አታ​ል​ቅሱ፤ አት​ዘ​ኑ​ለ​ትም።


እነሆ፥ ወደ አባ​ቶ​ችህ እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በሰ​ላ​ምም ወደ መቃ​ብ​ርህ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለህ፤ በዚ​ህም ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የማ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ ዐይ​ኖ​ችህ አያ​ዩም” ያለ​ቻ​ቸ​ው​ንም ነገር ለን​ጉሡ አስ​ረ​ዱት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ ከአ​ባ​ቶ​ችህ ጋር ታን​ቀ​ላ​ፋ​ለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነ​ሣል፤ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ዘንድ በሚ​ሄ​ድ​ባት ምድር መካ​ከል ያሉ​ትን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ትሎ ያመ​ነ​ዝ​ራል፤ እኔ​ንም ይተ​ወ​ኛል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ያፈ​ር​ሳሉ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ቃል መል​ካም ነው። ደግ​ሞም በዘ​መኔ ሰላም ይሁን” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios