Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 22:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እነ​ር​ሱም፦ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ስለ ሰገዱ፥ ስለ አመ​ለ​ኳ​ቸ​ውም ነው ብለው ይመ​ል​ሳሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም፣ ‘የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ኪዳን ትተው ሌሎችን አማልክት ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው’ ይላሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እነርሱም፦ “የአምላካቸውን የጌታን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ ስላገለገሉአቸውም ነዋ ብለው ይመልሳሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እናንተ ከእኔ ከአምላካችሁ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን አፍርሳችሁ ባዕዳን አማልክትን በማምለካችሁና በማገልገላችሁ ምክንያት መሆኑንም ይረዳሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እነርሱም፦ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ ስላመለኩአቸውም ነዋ ብለው ይመልሳሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 22:9
16 Referencias Cruzadas  

ከፍ ከፍ ብሎ የነ​በ​ረ​ውም ይህ ቤት ባድማ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ እያ​ፍ​ዋጨ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሀገ​ርና በዚህ ቤት ስለ ምን እን​ዲህ አደ​ረገ? ብሎ ይደ​ነ​ቃል።


በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ሁሉ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ትታ​ች​ሁ​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ዐጥ​ና​ች​ኋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፥ አይ​ጠ​ፋ​ምም።


በእ​ጃ​ቸው ሥራ ሁሉ ሊያ​ስ​ቈ​ጡኝ ትተ​ው​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት አጥ​ነ​ዋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋ​ምም።


ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ኀጢ​አት ተመ​ለሱ፥ ያመ​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን አፈ​ረሱ።


እን​ደ​ዚ​ህም በሏ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃል የማ​ይ​ሰማ ሰው ርጉም ይሁን፤


አንተ እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እኔን ስለ ተዉ ነው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ አመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም ትተ​ው​ኛል፤ ሕጌ​ንም አል​ጠ​በ​ቁም፤


ያገ​ኙ​አ​ቸው ሁሉ በሉ​አ​ቸው፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፦ በጽ​ድቅ ማደ​ሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ተስፋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ስለ ሠሩ እኛ አና​ሳ​ር​ፋ​ቸ​ውም አሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ ሕዝቤ በፊ​ታ​ቸው የሰ​ጠ​ኋ​ቸ​ውን ሕጌን ትተ​ዋል፤ ቃሌ​ንም አል​ሰ​ሙም።


በሚ​ሄ​ዱ​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ መካ​ከል ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይና​ገሩ ዘንድ ከሰ​ይ​ፍና ከራብ፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርም ጥቂ​ቶች ሰዎ​ችን ከእ​ነ​ርሱ አስ​ቀ​ራ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንና ሥራ​ቸ​ውን በአ​ያ​ችሁ ጊዜ ያጽ​ና​ኗ​ች​ኋል፤ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ት​ንም ሁሉ በከ​ንቱ እን​ዳ​ላ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ባት ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አሕ​ዛ​ብም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ምክ​ን​ያት እንደ ተማ​ረኩ ያው​ቃሉ፤ ስለ ከዱኝ እኔም ፊቴን ከእ​ነ​ርሱ ስለ መለ​ስሁ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፥ እነ​ር​ሱም ሁሉ በሰ​ይፍ ወደቁ።


በቍ​ጣ​ዬና በመ​ቅ​ሠ​ፍቴ በተ​በ​ቀ​ል​ሁሽ ጊዜ በዙ​ሪ​ያሽ በአሉ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ትጨ​ነ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ትደ​ነ​ግ​ጫ​ለ​ሽም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።


አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚ​ህች ምድር ስለ ምን እን​ደ​ዚህ አደ​ረገ? ይህስ የቍ​ጣው ታላቅ መቅ​ሠ​ፍት ምን​ድን ነው? ይላሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos