ያዕቆብ 5:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይ ተቀማጥላችኋል፤ በሴሰኝነትም ኖራችኋል፤ ለእርድ ቀን እንደሚያወፍር ልባችሁን አወፍራችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድርም ላይ በምቾትና በመቀማጠል ኖራችኋል፤ ለዕርድ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድርም ላይ በምቾትና በመቀማጠል በመኖር ለዕርድ ቀን እንደሚዘጋጅ ልባችሁን አወፍራችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምቾትና በደስታ በመኖር ልባችሁን ለዕርድ እንደ ተዘጋጀ ከብት አወፍራችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ ተቀማጥላችኋል በሴሰኝነትም ኖራችኋል፤ ለእርድ ቀን እንደሚያወፍር ልባችሁን አወፍራችኋል። |
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
እነሆም፥ በዓልን፥ ደስታንና ሐሴትን አደረጋችሁ፤ በሬዎችንና በጎችንም አረዳችሁ፤ “ነገ እንሞታለን፤ እንብላ፤ እንጠጣም፤” እያላችሁ ሥጋን በላችሁ፤ ወይንንም ጠጣችሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፥ “የጽዮን ቆነጃጅት ኰርተዋልና፥ አንገታቸውን እያሰገጉ በዐይናቸውም እያጣቀሱ፥ በእግራቸውም እያረገዱ፥ ልብሳቸውንም እየጐተቱ፥ በእግራቸውም እያማቱ ይሄዳሉና፤
አሁንም አንቺ ቅምጥል ተዘልለሽ የምትቀመጪ፥ በልብሽም፥ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም፤ የወላድ መካንነትንም አላውቅም” የምትዪ፥ ይህን ስሚ፤
ኑ፤ የወይን ጠጅ እንውሰድ፤ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፤ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል ይላሉ።
አንተ ግን አቤቱ! ዐውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፤ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፤ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፤ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።
ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደ የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች! አልቅሱ፤ እናንተም የበጎች አውራዎች! ጩኹ።
እነሆ የእኅትሽ የሰዶም ኀጢአት ይህ ነበረ፤ ትዕቢት፥ እንጀራን መጥገብ፥ መዝለልና ሥራን መፍታት፥ ይህ ሁሉ በእርስዋና በልጆችዋ ነበር፤ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሚበርሩ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊት ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ ኑ፤ ተከማቹ፤ ሥጋንም ትበሉ ዘንድ፥ ደምንም ትጠጡ ዘንድ በእስራኤል ተራሮች ላይ ወደማርድላችሁ መሥዋዕት፥ እርሱም ታላቅ መሥዋዕት፥ ከየሰፍራው ሁሉ ተሰብሰቡ።
አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ተድላና ደስታ እንዳደረግህ፥ አልዓዛርም እንዲሁ ሁልጊዜ በችጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እንዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድላና ደስታ ያደርጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀበላለህ።
በቀን እንደሚሆን በጽድቅ ሥራ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር፥ በዝሙትና በመዳራትም አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን።
የዐመፃቸውን ደመወዝ ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ ነውረኞችና ርኵሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤
እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥
ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ባልቴትም አልሆንም፤ ሐዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥
አቤግያም ወደ ናባል መጣች፤ እነሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደርግ ነበር፤ ናባልም እጅግ ሰክሮ ነበርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለዚህም እስኪነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አልነገረችውም ነበር።