Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 47:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አሁ​ንም አንቺ ቅም​ጥል ተዘ​ል​ለሽ የም​ት​ቀ​መጪ፥ በል​ብ​ሽም፥ “እኔ ነኝ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበ​ለ​ትም ሆኜ አል​ኖ​ርም፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ት​ንም አላ​ው​ቅም” የም​ትዪ፥ ይህን ስሚ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “አሁንም አንቺ ቅምጥል ፍጡር፣ በራስሽ ተማምነሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም፤ ከእንግዲህ መበለት አልሆንም፤ የወላድ መካንም አልሆንም’ የምትይ ስሚ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አሁንም አንቺ ተድላን የምትወጅ፥ በምቾትም የምትቀመጪ፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም፥ የወላድ መካንነትንም አላውቅም” የምትዪ ይህን ስሚ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “አንቺ በልብሽ ‘እንደ እኔ ያለ ማንም የለም፤ ባልዋ እንደ ሞተባት ሴት ሆኜ አልኖርም፤ ወይም የልጅ ሞት አይደርስብኝም’ ብለሽ በመዝናናት የተቀመጥሽው ቅምጥሊቱ ሆይ! ይህን ስሚ፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አሁንም አንቺ ቅምጥል ተዘልለሽ የምትቀመጪ፥ በልብሽም፦ እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፥ መበለትም ሆኜ አልኖርም የወላድ መካንነትንም አላውቅም የምትዪ ይህን ስሚ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 47:8
36 Referencias Cruzadas  

ተዘልላ የተቀመጠች፥ በልብዋም፦ እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ያለች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፣ አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ እንዴት ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፍዋጫል።


እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ሴቶች ሆይ፥ ተነሡ፤ ድም​ፄ​ንም ስሙ፤ እና​ንተ ተማ​ም​ና​ችሁ የም​ት​ቀ​መጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ንግ​ግ​ሬን አድ​ምጡ።


“ርስ​ቴን የም​ት​በ​ዘ​ብዙ እና​ንተ ሆይ! ደስ ብሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ ሐሤ​ት​ንም አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ በመ​ስክ ላይም እን​ዳ​ለች ጊደር ሆና​ችሁ ተቀ​ና​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ብር​ቱ​ዎ​ችም በሬ​ዎች ቷጋ​ላ​ች​ሁና፤


በክ​ፋ​ትሽ ታም​ነ​ሻል፤ አንቺ ግን፥ “እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ የለም” ብለ​ሻል፤ በዝ​ሙ​ትሽ ኀፍ​ረት ያሰ​ብ​ሽ​ው​ንም ዕወቂ፤ በል​ብሽ፥ “እኔ ነኝ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም” ብለ​ሻ​ልና።


በፀ​ሐይ መው​ጫና በም​ዕ​ራብ ያሉ ከእኔ በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ያውቁ ዘንድ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም ሌላ አም​ላክ የለም።


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።


እርስ በእርሳቸው እንደ ተመሰቃቀለ እሾህ ቢሆኑ፥ በመጠጣቸውም ቢሰክሩ እንደ ደረቅ ገለባ ፈጽመው ይጠፋሉ።


ባቢ​ሎ​ንም ወደ ሰማይ ብት​ወጣ፥ ቅፅ​ሮ​ች​ዋ​ንም በኀ​ይ​ልዋ ብታ​ጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥ​ፊ​ዎች ይመ​ጡ​ባ​ታል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰማ​ይን የፈ​ጠረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እር​ሱም ምድ​ርን የሠ​ራና ያደ​ረገ ያጸ​ና​ትም፥ መኖ​ሪ​ያም ልት​ሆን እንጂ ለከ​ንቱ እን​ድ​ት​ሆን ያል​ፈ​ጠ​ራት አም​ላክ፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም።


እነ​ር​ሱም ሚካ የሠ​ራ​ውን ጣዖ​ትና ለእ​ርሱ የነ​በ​ረ​ውን ካህን ይዘው ወደ ሌሳ፥ ጸጥ ብሎ ተዘ​ል​ሎም ወደ ተቀ​መ​ጠው ሕዝብ መጡ፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት።


አም​ስ​ቱም ሰዎች ሄዱ፤ ወደ ሌሳም ደረሱ፤ በው​ስ​ጡም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ተዘ​ል​ለው አዩ​አ​ቸው፤ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም ልማድ ጸጥ ብለው፥ ዐር​ፈው፥ ተዘ​ል​ለ​ውም ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ በተ​መ​ዘ​ገ​በች የር​ስ​ታ​ቸው ምድ​ርም ቃልን መና​ገር አል​ቻ​ሉም፤ ከሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንም ርቀው ይኖሩ ነበር። ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ጋር ግን​ኙ​ነት አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።


ከደ​መ​ና​ዎች ከፍታ በላይ ዐር​ጋ​ለሁ፤ በል​ዑ​ልም እመ​ሰ​ላ​ለሁ አልህ።


እና​ንተ ተማ​ም​ና​ችሁ የም​ት​ቀ​መጡ ደን​ግጡ፤ ሴቶች ሆይ፥ እዘኑ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም አው​ልቁ፤ ዕራ​ቁ​ታ​ች​ሁ​ንም ሁኑ፤ ወገ​ባ​ች​ሁ​ንም በማቅ ታጠቁ።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ አጸ​ና​ሁህ፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም።


“ተነሡ፤ ዕረ​ፍት ወዳ​ለ​በት፥ ተዘ​ል​ሎም ወደ ተቀ​መ​ጠው፥ ደጅና መዝ​ጊያ፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያም ወደ​ሌ​ለው፥ ብቻ​ው​ንም ወደ ተቀ​መ​ጠው ሕዝብ ዝመቱ።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢ​ሮ​ስን አለቃ እን​ዲህ በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብህ ኰር​ት​ዋል፥ አንተ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕር መካ​ከል እን​ዲ​ቀ​መጥ እኔም ተቀ​ም​ጫ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ አንተ ሰው ስት​ሆን ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ ብታ​ደ​ር​ግም አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።


በዚያ ቀን መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተዘ​ል​ለው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንን ለማ​ጥ​ፋት ከፊቴ በመ​ር​ከብ ይወ​ጣሉ፤ በግ​ብ​ፅም ቀን ሁከት ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ እነሆ፥ ይመ​ጣ​ልና።


እነሆ የእ​ኅ​ትሽ የሰ​ዶም ኀጢ​አት ይህ ነበረ፤ ትዕ​ቢት፥ እን​ጀ​ራን መጥ​ገብ፥ መዝ​ለ​ልና ሥራን መፍ​ታት፥ ይህ ሁሉ በእ​ር​ስ​ዋና በል​ጆ​ችዋ ነበር፤ የች​ግ​ረ​ኛ​ው​ንና የድ​ሀ​ው​ንም እጅ አላ​ጸ​ና​ችም።


ስለ ተዋበችው ጋለሞታ ግልሙትና ብዛት ይህ ሆኖአል፣ እርስዋም በመተትዋ እጅግ በለጠች፥ አሕዛብንም በግልሙትናዋ፥ ወገኖችንም በመተትዋ ሸጠች።


እነርሱ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፣ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios