Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 25:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ደኅ​ን​ነ​ትና ሰላም ለአ​ን​ተና ለቤ​ትህ፥ ለአ​ን​ተም ለሆ​ኑት ሁሉ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እንዲህም በሉት፤ ‘ዕድሜህ ይርዘም! ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ሰላም ለቤተ ሰብህና የአንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እንዲህም በሉት፤ ‘ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ሰላም ለቤተሰብህና የአንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ለናባልም ይነግሩት ዘንድ እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጣቸው፦ “ሰላም ላንተ፥ ሰላም ለቤትህ፥ ሰላም ያንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን ብላችሁ ሰላምታ አቅርቡለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በደኅንነት ኑር፥ ለአንተና ለቤትህም ለአንተም ላሉት ሁሉ ሰላም ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 25:6
12 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም አላ​ቸው፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፥ አት​ፍሩ፤ አም​ላ​ካ​ችሁ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ የተ​ሰ​ወረ ገን​ዘብ ሰጣ​ችሁ፤ ብራ​ች​ሁ​ንስ መዝኜ ተቀ​ብ​ያ​ለሁ።”


አኪ​ማ​ሖ​ስም ጮኾ ንጉ​ሡን፥ “ሰላም ለአ​ንተ ይሁን!” አለው። በን​ጉ​ሡም ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ሰግዶ፥ “በን​ጉሡ በጌ​ታዬ ላይ እጃ​ቸ​ውን ያነ​ሡ​ትን ሰዎች አሳ​ልፎ የሰጠ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።


መን​ፈ​ስም በሠ​ላ​ሳው አለቃ በዓ​ማ​ሣይ ላይ መጣ፤ እር​ሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእ​ሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአ​ንተ ጋር ነን፤ ውጣ አም​ላ​ክህ ይረ​ዳ​ሃ​ልና ሰላም ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ ለሚ​ረ​ዱ​ህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊ​ትም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ የጭ​ፍ​ራም አለ​ቆች አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ወደ ገባ​ች​ሁ​በት ቤትም አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ‘ለዚህ ቤት ሰዎች ሰላም ይሁን’ በሉ።


“ሰላ​ምን እተ​ው​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሰላ​ሜ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ሰ​ጣ​ችሁ ዓለም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጠው አይ​ደ​ለም፤ ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ፍ​ሩም።


እናንተ በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ፥ አሁን በሕይወት እንኖራለንና።


የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።


ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት።


ዳዊ​ትም ዐሥር ብላ​ቴ​ኖ​ችን ላከ፤ ለብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አለ፥ “ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወጥ​ታ​ችሁ ወደ ናባል ሂዱ፤ በስ​ሜም ሰላም በሉት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos