Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ምሳሌ 7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ፥ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ።

2 ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርን አክብረው ትጸናለህም። ከእርሱ በቀር ሌላውን አትፍራ፥ ከእርሱ በቀር የሚገድልህም የሚያድንህም የለምና። ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፤ ቃሌንም እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቅ፤

3 በጣቶችህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላትም ጻፋቸው።

4 ጥበብን፦ “አንቺ እኅቴ ነሽ” በላት፥ ማስተዋልንም፦ “ወዳጄ” ብለህ ጥራት፥

5 ከባዕድና ከክፉ ሴት ዋዛ ነገርንም ከምታመጣብህ ትጠብቅህ ዘንድ።


ስለ አመንዝራ ሴት አታላይነት

6 በቤትWa መስኮት ሆና ወደ ዐደባባይ ትመለከታለችና፤

7 ከአላዋቂዎች ወጣቶች መካከል ከዕውቅት ድሃ የሆነውን ጐልማሳ ብታይ፥

8 በቤቷም አቅራቢያ ባለው መንገድ ሲሄድ ሲናገርም፤

9 ማታ ሲመሽ፥ ውድቅትም ሲሆን፥ በሌሊት በጽኑ ጨለማ፥

10 የምንዝር ጌጥ ያላት የጐልማሶችን ልብ እንዲሰቀል የምታደርግ ሴት ያንጊዜ ትገናኘዋለች። እርስዋ የምትበርር መዳራትንም የምትወድ ናት።

11 ሁከተኛና አበያ ናት፥ እግሮችዋም በቤቷ አያርፉም፥

12 አንድ ጊዜ በጎዳና፥ በሌላ ጊዜም በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች።

13 ያዘችውም ሳመችውም፤ ፊቷም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦

14 “የፍቅሬ መሥዋዕት ነው፤ ዛሬ ስእለቴን እሰጣለሁ።

15 ስለዚህ እንድገናኝህ መጣሁ፥ ፊትህንም ለማየት ስሻ አገኘሁህ።

16 በአልጋዬ ላይ ማለፊያ ሰርፍ ዘርግቼበታለሁ፥ የግብፅንም ሸመልመሌ ምንጣፍ።

17 በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ።

18 ና፥ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ። በመልካም መተቃቀፍም ደስ ይበለን።

19 ባለቤቴ በቤቱ የለምና፥ ወደ ሩቅ መንገድ ሄዶአልና፤

20 በእጁም የወርቅ ከረጢት ይዞአል፤ ወደ ቤቱ ቢመለስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው።”

21 በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፤ በከንፈርዋ ወጥመድም ትጐትተዋለች።

22 እርሱ አንገቱን ደፍቶ ይከተላታል፥ ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ፥ ወደ እስራት እንደሚሄድ ውሻ፥ ሆዱ እንደ ተወጋ ዋሊያ፥

23 ወደ ወጥመድ እንደሚቸኩል ዎፍ፥ ሳያውቅም ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሮጥ።

24 ልጄ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስማኝ፥ ወደ አፌ ቃል አድምጥ።

25 ልብህ ወደ መንገድዋ አያዘንብል፤ በጎዳናዋ አትሳት።

26 ብዙዎችን ወግታ አስታለች፤ እርስዋም የገደለቻቸው ቍጥር የላቸውም።

27 ቤቷ ወደ ሞት ጓዳ የሚያወርድ የሲኦል መንገድ ነው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos