አለውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ታግለህ በርትተሃልና።”
ኢሳይያስ 48:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፥ ከይሁዳም የወጣችሁ፥ በእውነት ሳይሆን፥ በጽድቅም ሳይሆን እርሱን እየጠራችሁ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፣ ከይሁዳ ዘር የተገኛችሁ፣ እናንተ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፣ በእውነት ወይም በጽድቅ ሳይሆን፣ የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ ይህን ስሙ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ ከይሁዳም ውኆች የወጣችሁ፥ በጌታ ስም የምትምሉ፥ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእስራኤል ስም የምትጠሩ፥ ከይሁዳ ወገን የሆናችሁ፥ እናንተ የያዕቆብ ልጆች! ይህን ስሙ። እናንተ በታማኝነትና በእውነት ሳይሆን፥ የእስራኤልን አምላክ እናመልካለን ትላላችሁ፤ በእግዚአብሔር ስምም ትምላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ ከይሁዳም ውኆች የወጣችሁ፥ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፥ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ፥ |
አለውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ታግለህ በርትተሃልና።”
እስከ ዛሬም ድረስ እንደ ልማዳቸው ያደርጋሉ፤ እግዚአብሔርንም ይፈራሉ፤ እግዚአብሔርም እስራኤል ብሎ የጠራውን የያዕቆብን ልጆች እንዳዘዛቸው ሥርዐትና ፍርድ፥ ሕግና ትእዛዝም ያደርጋሉ።
የኤልሳዕም ሎሌ ግያዝ፥ “ጌታዬ ሶርያዊውን ይህን ንዕማንን ማረው፤ ካመጣለትም ነገር ምንም አልተቀበለም፤ ሕያው እግዚአብሔርን! በስተኋላው እሮጣለሁ፤ ከእርሱም አንዳች እወስዳለሁ” አለ።
ይህ፦ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ይላል፤ ያም በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ይህም፦ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽፋል፤ በእስራኤልም ስም ይጠራል።”
ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፤ አትመለስምም፤ ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ በእግዚአብሔር ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።”
እናንተ ጽድቅን የምትከተሉ እግዚአብሔርንም የምትሹ፥ ስሙኝ፤ የተቈረጣችሁበትን ጽኑዕ ዓለት የተቈፈራችሁባትንም ጥልቅ ጕድጓድ ተመልከቱ።
ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፤ ባረክሁትም፤ ወደድሁትም፤ አበዛሁትም።
ነገር ግን ጽድቅን እንደሚያደርግ የአምላኩንም ፍርድ እንደማይተው ሕዝብ ዕለት ዕለት ይሹኛል፤ መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ። አሁንም እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል፤ ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ።
እግዚአብሔር፥ “ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፥ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም፤” ብሎ በጌትነቱና በክንዱ ኀይል ምሎአል።
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ በኀጢአታችን ምክንያት እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ እንዲሁም ነፋስ ጠራርጎ ወስዶናል።
እንዲሁም በምድር ላይ የተባረኩ ይሆናሉ፤ እውነተኛውን አምላክ ያመሰግናሉና፥ በምድርም ላይ በእውነተኛው አምላክ ይምላሉና፤ የቀድሞውንም ጭንቀት ረስተዋልና፤ በልቡናቸውም አያስቡትምና።
ሕያው እግዚአብሔርን! ብሎ በእውነትና በቅንነት፤ በጽድቅም ቢምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ፤ በኢየሩሳሌምም እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።
ስለዚህ እናንተ በግብፅ ምድር የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ በታላቁ ስሜ ምያለሁ፥” ይላል እግዚእብሔር።
የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚያች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን?
እንዲህም አለኝ፦ ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፣ የሚሰርቅ ሁሉ በእርሱ ላይ በዚህ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል፥ በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእርሱ ላይ በዚያ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ልጆች እንዲሆኑት ተስፋ ያናገረለት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፤ እነዚህ ከሥጋ የተወለዱ ግን የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም።
እስራኤልም ተማምኖ፥ በያዕቆብ ምድር ብቻውን፥ በስንዴና በወይን ምድር ይኖራል፤ ሰማይ ከደመናና ከጠል ጋር ለአንተ ነው።
“በተናገራችሁኝም ጊዜ እግዚአብሔር የእናንተን ቃል ድምፅ ሰማ፤ እግዚአብሔርም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ የተናገሩህን ቃል ድምፅ ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩህ ሁሉ ትክክል ነው።
“መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።