ኢሳይያስ 26:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ክንድህ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ ለሕዝብህ ያለህን ቅናት ይዩ፤ ይፈሩም፤ ለጠላቶችህም የተዘጋጀው እሳት ይብላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ ጌታ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩምም፥ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፥ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች። |
በምድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እንደሌለ ታውቅ ዘንድ በሰውነትህ፥ በአገልጋዮችህም፥ በሕዝብህም ላይ መቅሠፍቴን ሁሉ በዚህ ጊዜ እልካለሁ።
ኀይላቸውም እንደ መቃ መስዬ፥ ሥራቸውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፤ ኃጥአንና ዐማፅያንም አብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋላቸው ያጣሉ።”
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በክብርህ ላይ ውርደትን፥ በጌጥህ ላይም የሚነድና የሚያቃጥል እሳትን ይሰድዳል።
የኤፍሬምም ቅናት ይሻራል፤ የይሁዳም ጠላቶች ይጠፋሉ፤ ኤፍሬምም በይሁዳ አይቀናም፤ ይሁዳም ኤፍሬምን አያስጨንቅም።
ከኢየሩሳሌም ቅሬታ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይድናሉና፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንአት ይህን ያደርጋል።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይወጣል፤ ኀይለኛውንም ያጠፋል፤ ቅንአትንም ያስነሣል፤ በጠላቶቹም ላይ በኀይል ይጮኻል።
ጣዖታትን የሚቀርጹ ያንጊዜ አይኖሩም፤ የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩም ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ የማይረባቸውን የራሳቸውን ፍላጎት የሚያደርጉ ሁሉ ያፍራሉ።
ስለዚህ ገለባ በእሳት ፍም እንደሚቃጠል፥ በነበልባልም እንደሚበላ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፤ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።
የአስጨናቂዎችሽም ልጆች እየተንቀጠቀጡ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብለሽም ትጠሪያለሽ።
ከሰማይ ተመለስ፤ ከቅድስናህና ከክብርህ ማደሪያም ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህስ ወዴት ነው? የቸርነትህና የይቅርታህ ብዛት ወዴት ነው? ቸል ብለሃልና።
እነሆ፥ እግዚአብሔር መዓቱን በቍጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ እንደ እሳት ይመጣል፤ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።
ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸውም አይጠፋም፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ ምሳሌ ይሆናሉ።”
በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ “የእግዚአብሔር ስም ይከብር ዘንድ፦ ደስታችሁም ይገለጥ ዘንድ፥ እነርሱም ያፍሩ ዘንድ የሚጠሏችሁንና የሚጸየፉአችሁን ወንድሞቻችን በሏቸው።
ኀጢአት እንደ እሳት ይነድዳል፤ እሳት እንደ በላችው ደረቅ ሣር ይቃጠላል፤ እንደ ዱር ሣርም ይቃጠላል፤ በተራራዎች ዙሪያ ያለው ሁሉ አብሮ ይቃጠላል።
በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ሁሉ ትቃጠላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም።
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
ከሰይፍም የሚያመልጡ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች ከግብፅ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ፤ ሊቀመጡም ወደ ግብፅ ምድር የገቡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማናችን ቃል እንዲጸና ያውቃሉ።
አቤቱ! ዐይኖችህ ለሃይማኖት አይደሉምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፤ ነገር ግን አላዘኑም፤ ቀጥቅጠሃቸውማል፤ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱም ዘንድ እንቢ አሉ።
እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ወደ እኔም እንዳይመለሱና ይቅር እንዳልላቸው የዚህ ሕዝብ ልባቸው ደንድኖአልና፥ ጆሮአቸውም ደንቁሮአልና፥ ዐይናቸውንም ጨፍነዋልና’።
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።
ወደምትሄድበትም ተመልከቱ፤ በድንበሩም መንገድ ላይ ወደ ቤትሳሚስ ብትወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደረገብን እርሱ ነው፤ አለዚያም እንዲያው መጥቶብናል እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን።”