Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 18:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ይቀ​መ​ጣሉ፤ ከተ​ራ​ሮች ራሶ​ችም እንደ ዓላማ ይይ​ዙ​ታል፤ እንደ መለ​ከት ድም​ፅም ይሰ​ማል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እናንተ የዓለም ሕዝቦች፣ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፣ በተራሮች ላይ ምልክት ሲሰቀል ታዩታላችሁ፤ መለከትም ሲነፋ ትሰሙታላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እናንት በዓለም ውስጥ ያላችሁና በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሆይ፥ ምልክት በተራሮች ላይ በሚወጣ ጊዜ ተመልከቱ! መለከትም በተነፋ ጊዜ ስሙ!

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በምድር የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ! በተራሮች ጫፍ ላይ የተተከለ የሰንደቅ ዓላማ ምልክት ሲውለበለብ አስተውሉ! መለከት ሲነፋ ስሙ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በዓለም የምትኖሩ ሁሉና በምድር የምትቀመጡ ሆይ፥ ምልክት በተራሮች ላይ በተነሣ ጊዜ እዩ፥ መለከትም በተነፋ ጊዜ ስሙ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 18:3
20 Referencias Cruzadas  

በሩቅ ላሉ አሕ​ዛ​ብም ምል​ክ​ትን ያቆ​ማል፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ በፉ​ጨት ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ እየ​ተ​ጣ​ደፉ ፈጥ​ነው ይመ​ጣሉ።


አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክን​ድ​ህን አላ​ወ​ቁም፤ ካወቁ ግን ያፍ​ራሉ። አላ​ዋ​ቆች ሰዎ​ችን ቅን​አት ያዛ​ቸው፤ አሁ​ንም እሳት ጠላ​ቶ​ችን ትበ​ላ​ለች።


የእናንተ ግን ዐይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።


የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”


እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።


የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፥ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፥ የመቅሠፍትን በትር፥ እርሱንም ያዘጋጀ ማን እንደ ሆነ ስሙ።


ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።


ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሚ።


በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተ​ሰ​በ​ሰቡ ነገ​ሥ​ታ​ትና የአ​ሕ​ዛብ ድም​ፅም አለ። የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተዋ​ጊ​ዎች አሕ​ዛብ ይመጡ ዘንድ አዘዘ።


ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምል​ክ​ትን አቁሙ፤ ድም​ፃ​ች​ሁ​ንም ከፍ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ አለ​ቆች በእጅ ጥቀሱ። በሮ​ች​ንም ክፈቱ።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ወንዝ ዳርቻ ያለ​ውን ዝንብ፥ በአ​ሦ​ርም ሀገር ያለ​ውን ንብ በፉ​ጨት ይጠ​ራል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድ​ርም አድ​ምጪ፤ ልጆ​ችን ወለ​ድሁ፤ አሳ​ደ​ግ​ሁም፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፁ​ብኝ።


አቤቱ፥ እንደ ቸር​ነ​ትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ኀጢ​አ​ቴን ደም​ስስ።


ዓለ​ትም ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች ድልም ይሆ​ናሉ የሸ​ሸም ይያ​ዛል። በጽ​ዮን ዘርእ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቤቶች ያሉት ብፁዕ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ እጄን ወደ አሕ​ዛብ አነ​ሣ​ለሁ፤ ዓር​ማ​ዬ​ንም ወደ ደሴ​ቶች አቆ​ማ​ለሁ፤ ወን​ዶች ልጆ​ች​ሽ​ንም በብ​ብ​ታ​ቸው ታቅ​ፈው ያመ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ሴቶች ልጆ​ች​ሽ​ንም በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል።


“በም​ድር ላይ ዓላ​ማን አንሡ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል መለ​ከ​ትን ንፉ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ለዩ​ባት፤ የአ​ራ​ራ​ት​ንና የሚ​ኒን የአ​ስ​ከ​ና​ዝ​ንም መን​ግ​ሥ​ታት እዘ​ዙ​ባት፤ ጦረ​ኞ​ች​ንም በላ​ይዋ አቁሙ፤ ብዛ​ታ​ቸው እንደ አን​በጣ የሆኑ ፈረ​ሶ​ችን በላ​ይዋ አውጡ።


እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ ስሙ፥ ምድርም ሙላዋም ታድምጥ፥ ጌታ እግዚአብሔርም፥ እርሱም በቅዱስ መቅደሱ የሆነ ጌታ፥ ይመስክርባችሁ።


ለአ​ሕ​ዛ​ብም ምል​ክ​ትን ያቆ​ማል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የቀ​ሩ​ትን ይሰ​በ​ስ​ባል፤ ከይ​ሁ​ዳም የተ​በ​ተ​ኑ​ትን ከአ​ራቱ የም​ድር ማዕ​ዘ​ኖች ያከ​ማ​ቻል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios