Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 66:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እናንተ በቃሉ የምትንቀጠቀጡ፣ ይህን የእግዚአብሔር ቃል ስሙ፤ “እናንተ ወንድሞቻችሁ የጠሏችሁ፣ ስለ ስሜም አውጥተው የጣሏችሁ፣ ‘እስኪ እግዚአብሔር ይክበርና፣ የእናንተን ደስታ እንይ!’ አሏችሁ፤ ይሁን እንጂ ማፈራቸው አይቀርም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እናንት በቃሉ ፊት የምትርዱ፥ የጌታን ቃል ስሙ፦ የጠሉአችሁ የናንተው ሕዝብ፥ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ፦ “ደስታችሁን እንድናይ ጌታ ይክበር” ብለዋል፤ ነገር ግን ያፍራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ቃሉን የምታከብሩ እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ “ስለ ስሜ የሚጠሉአችሁና የሚያገሉአችሁ እንዲህ ይሉአችኋል፦ ‘እናንተ ስትደሰቱ እናይ ዘንድ እስቲ እግዚአብሔር ክብሩን ይግለጥ፤’ ኀፍረት ላይ የሚወድቁት ግን እነርሱ ራሳቸው ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ፦ ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር ብለዋል፥ ነገር ግን ያፍራሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 66:5
32 Referencias Cruzadas  

ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ወደ የዋ​ሁና ወደ ጸጥ​ተ​ኛው፥ ከቃ​ሌም የተ​ነሣ ወደ​ሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ ሰው ከአ​ል​ሆነ በቀር ወደ ማን እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ?


በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “ራስህ በኀ​ጢ​ኣት የተ​ወ​ለ​ድህ አንተ እኛን ታስ​ተ​ም​ረ​ና​ለ​ህን?” አሉት፤ ወደ ውጭም አወ​ጡት።


እን​ዲ​ህም ሆነ፦ ቃሉን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈር​ተው እርስ በር​ሳ​ቸው ተመ​ካ​ከሩ፤ ባሮ​ክ​ንም፥ “ይህን ቃል ሁሉ በር​ግጥ ለን​ጉሡ እን​ና​ገ​ራ​ለን” አሉት።


“እናይ ዘንድ፥ ሥራ​ውን ያፋ​ጥን፤ እና​ው​ቃ​ትም ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ምክር፥ ትምጣ” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው!


ፀሓይ መል​ኬን አክ​ስ​ሎ​ታ​ልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አት​ዩኝ፤ የእ​ናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፥ የወ​ይን ቦታ​ዎ​ች​ንም ጠባቂ አደ​ረ​ጉኝ፤ ነገር ግን የእ​ኔን የወ​ይን ቦታ አል​ጠ​በ​ቅ​ሁም።


ወንድሞች ሆይ፥ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ።


ይህ​ንም ባለ ጊዜ በእ​ርሱ ላይ በጠ​ላ​ት​ነት የተ​ነ​ሡ​በት ሁሉ አፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከእ​ርሱ ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላ​ቸው።


የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያቃልለውን እርሱ ያቃልለዋል፥ ትእዛዙን የሚሰማ ግን በእርሱ በሕይወት ይኖራል። ለውሸተኛ ልጅ ምንም ደግነት የለም፥ ለብልህ አገልጋይ ግን ሥራው መልካም ይሆናል። መንገዱም ይቃናል።


እን​ዲሁ ክር​ስ​ቶ​ስም የብ​ዙ​ዎ​ችን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ር​ጉት ያለ ኀጢ​አት ይገ​ለ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል።


ከም​ኵ​ራ​ባ​ቸው ያስ​ወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ ደግ​ሞም እና​ን​ተን የሚ​ገ​ድ​ላ​ችሁ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ያ​ቀ​ርብ የሚ​መ​ስ​ል​በት ጊዜ ይመ​ጣል።


የተ​ተ​ው​ሽና የተ​ጠ​ላሽ ሆነ​ሻ​ልና የሚ​ረ​ዳሽ አጣሽ፤ ነገር ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታን ለልጅ ልጅ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ይበ​ላሉ፤ እና​ንተ ግን ትራ​ባ​ላ​ችሁ፤ እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ይጠ​ጣሉ፤ እና​ንተ ግን ትጠ​ማ​ላ​ችሁ፤ እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ትጐ​ሰ​ቍ​ላ​ላ​ችሁ፤


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እከ​ተ​ለው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እርሱ ያድ​ነ​ና​ልና፤ እር​ሱም እንደ አን​በሳ ያገ​ሣል፤ የውኃ ልጆ​ችም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


እነ​ዚ​ህም በእ​ነ​ዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ተጋ​ጠሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሶ​ር​ያ​ው​ያን በአ​ንድ ቀን መቶ ሺህ እግ​ረኛ ገደሉ።


ጸሓ​ፊው ሳፋ​ንም ለን​ጉሡ፥ “ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ የሕግ መጽ​ሐፍ ሰጥ​ቶ​ኛል” ብሎ ነገ​ረው። ሳፋ​ንም በን​ጉሡ ፊት አነ​በ​በው።


በፊ​ቴም ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ በዚ​ህም ስፍራ በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ቃሌን በሰ​ማህ ጊዜ ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህ​ንም ቀድ​ደህ በፊቴ አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ ምር​ኮ​ኞ​ቹም መተ​ላ​ለፍ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ቃል የሚ​ፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥ​ዋ​ዕት ድረስ ዐዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ።


አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክን​ድ​ህን አላ​ወ​ቁም፤ ካወቁ ግን ያፍ​ራሉ። አላ​ዋ​ቆች ሰዎ​ችን ቅን​አት ያዛ​ቸው፤ አሁ​ንም እሳት ጠላ​ቶ​ችን ትበ​ላ​ለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios