ኢሳይያስ 23:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክቡራንን ትዕቢት ይሽር ዘንድ፥ የምድርንም ክቡራን ሁሉ ያዋርድ ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊያዋርድ፣ በምድር ከፍ ከፍ ያለውንም ሁሉ ዝቅ ሊያደርግ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኗል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊሽር፥ የምድርንም ክብር ሁሉ ሊያስንቅ የሠራዊት ጌታ ይህን ወስኗል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንማ ያቀደው የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱም ይህን ያቀደው ባደረጉት ነገር መታበያቸውን እንዲተዉ ለማድረግና የተከበሩትንም ሰዎች ለማዋረድ ብሎ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የክብርን ሁሉ ትዕቢት ይሽር ዘንድ የምድርንም ክቡራን ሁሉ ያስንቅ ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖታል። |
እነሆ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክቡራንን በኀይል ያውካቸዋል፤ ታላላቆችንም በሐሣር ይቀጠቅጣቸዋል፤ ከፍ ያሉትም ይዋረዳሉ።
በዓለም ሁሉ ላይ ክፋትን አዝዛለሁ፤ የኀጢአተኞችንም ኀጢአት እጐበኛለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኵራት እሽራለሁ፤ የጨካኞቹንም ኵራት አዋርዳለሁ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፥ “እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፤ እንደ መከርሁም እንዲሁ ይጸናል።
ቅዱስ እግዚአብሔር ይህን መክሮአል፤ የእግዚአብሔርን ምክር የሚመልስ ማን ነው? የተዘረጋች እጁንስ የሚመልሳት ማን ነው?
የትዕቢተኞች ሰዎች ዐይኖች ይዋረዳሉ፤ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፤ እነርሱም ይዋረዳሉ፤
አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፥ ለዘለዓለምም ባድማ እንድትሆን ታጠፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተናግረሃል በል።
እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።