Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 10:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክቡ​ራ​ንን በኀ​ይል ያው​ካ​ቸ​ዋል፤ ታላ​ላ​ቆ​ች​ንም በሐ​ሣር ይቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ከፍ ያሉ​ትም ይዋ​ረ​ዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እነሆ፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በታላቅ ኀይል ቅርንጫፎችን ይቈራርጣል፤ ረዣዥም ዛፎች ይገነደሳሉ፤ ከፍ ከፍ ያሉትም ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እነሆ፥ ልዑል እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ፤ በታላቅ ኃይል ቅርንጫፎችን ይቈራርጣል፤ ረጃጅም ዛፎች ይገነደሳሉ፤ ከፍ ከፍ ያሉትም ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እነሆ የሠራዊት አምላክ ከዛፍ እንደ ተቈረጠ ቅርንጫፍ እየሰባበረ ያወርዳቸዋል፤ በእነርሱ መካከል ኩራተኛ የሆነውና እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ የታበየው ይዋረዳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እነሆ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅርንጫፎቹን በሚያስፈራ ኃይል ይቈርጣል፥ በቁመት የረዘሙትም ይቈረጣሉ፥ ከፍ ያሉትም ይዋረዳሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 10:33
17 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አ​ኩን ላከ፤ እር​ሱም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ኑ​ንና መሳ​ፍ​ን​ቱን አለ​ቆ​ቹ​ንም ከአ​ሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአ​ሦ​ርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ። ወደ አም​ላ​ኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወ​ገቡ የወ​ጡት ልጆቹ በዚያ በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።


እርሱ ከመ​ከር በፊት አበባ በረ​ገፈ ጊዜ የወ​ይ​ንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወ​ይ​ኑን ቀጫ​ጭን ዘንግ በማ​ጭድ ይቈ​ር​ጣል፤ ጫፎ​ቹ​ንም ይመ​ለ​ም​ላል፤ ያስ​ወ​ግ​ድ​ማል።


በረዶ ቢወ​ርድ አይ​ደ​ር​ስ​ባ​ች​ሁም፤ በዛፍ ሥር የሚ​ኖሩ ሰዎች በበ​ረሃ እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች ታም​ነው ይኖ​ራሉ።


ከቃ​ልህ ግርማ የተ​ነሣ አሕ​ዛብ ፈር​ተው ሸሹ፤ አሕ​ዛ​ብም ተበ​ተኑ።


በአ​ም​ላ​ኩም በና​ሳ​ራክ ቤት ሲሰ​ግድ ልጆቹ አድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ሳራ​ሳር በሰ​ይፍ ገደ​ሉት፤ ወደ አራ​ራ​ትም ሀገር ኰበ​ለሉ። ልጁም አስ​ራ​ዶን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


ታናሹ ሰውም ይጐ​ሰ​ቍ​ላል፤ ታላቁ ሰውም ይዋ​ረ​ዳል፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችም ዐይ​ኖች ይዋ​ረ​ዳሉ፤


የሚ​አ​ጠ​ፋ​ህን ሰው በአ​ንተ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ዛፍ​ህ​ንም በም​ሳር ይቈ​ር​ጣል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ላል።


እነሆ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍ​ግ​ነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመ​ቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም ወደ ደመ​ና​ዎች እንደ ደረሰ እንደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ነበረ።


እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብር​ታ​ቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነ​በ​ረ​ውን አሞ​ራ​ዊ​ውን ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋሁ፤ ፍሬ​ው​ንም ከላዩ፥ ሥሩ​ንም ከታቹ አጠ​ፋሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኃይለኞችና ብዙዎች ቢሆኑ እንዲሁ ይቈረጣሉ፥ እርሱም ያልቃል። እኔም አስጨንቄሃለሁ፥ ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አላስጨንቅህም።


ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos