ኢሳይያስ 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የትዕቢተኞች ሰዎች ዐይኖች ይዋረዳሉ፤ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢተኞች ይዋረዳሉ፤ ኩራተኞችም ይቀላሉ፤ እግዚአብሔር ብቻ በክብር ከፍ ከፍ ይላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፍ ያለችውም የሰው ዓይን ትዋረዳለች፥ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል። |
ስለዚህ እንዲህ ይሆናል፤ ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ የአሦርን ንጉሥ የኵሩ ልብን ፍሬ፥ የዐይኑንም ከፍታ ትምክሕት ይቀጣል።
በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ ዳግመኛም ይቅር ብለኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፥ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስታውሱ።
በዓለም ሁሉ ላይ ክፋትን አዝዛለሁ፤ የኀጢአተኞችንም ኀጢአት እጐበኛለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኵራት እሽራለሁ፤ የጨካኞቹንም ኵራት አዋርዳለሁ።
በዚያም ቀን፥ “እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፤ ያድናልም፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በመዳናችንም ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን” ይላሉ።
በዚያም ቀን ይህን ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘምራሉ፤ እነሆም፥ የጸናችና የምታድን፥ ቅጥርንና ምሽግንም የምታደርግ ከተማ አለችን።
አምላካችን እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፤ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
በምድርም ለተዘራው ዘርህ ዝናም ይዘንማል፤ ከምድርም ፍሬ የሚወጣ እንጀራ ወፍራምና ብዙ ይሆናል። በዚያም ቀን ከብቶችህ በሰፊና በለመለመ መስክ ይሰማራሉ፤
የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማንን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግህበት፥ ዐይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን?
በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፥ “የገዛ እንጀራችንን እንበላለን፤ የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፤ መሰደባችንንም አርቅልን” ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።
ርስቴ እንደ ጅብ ጕድጓድ ናትን? ወይስ በዙሪያዋ የሚከቡአት የሽፍቶች ዋሻ ናትን? የምድር አራዊት ሁሉ ይበሉአት ዘንድ ተሰብስበው ይመጣሉ።
ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግዚአብሔር።
አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ ጎግንም እንዲህ በለው፥ “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል በሰላም በተቀመጠ ጊዜ አንተ የምትነሣ አይደለምን?
“በዚያም ቀን በእስራኤል ዘንድ በባሕር ምሥራቅ የሚያልፉበትን ሸለቆ፥ የመቃብርን ስፍራ ለጎግ እሰጣለሁ፤ የሚያልፉትንም ይከለክላል፤ በዚያም ጎግንና ሠራዊቱን ሁሉ ይቀብራሉ፤ የሸለቆውንም ስም የጎግ መቃብር ብለው ይጠሩታል።
በዚያም ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፥ ከመሬትም ተንቀሳቃሾች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ። ቀስትንና ሰይፍን፥ ጦርንም ከምድሩ እሰብራለሁ፤ ተዘልለሽም ትቀመጫለሽ።
“በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ተራሮች ማርን ያንጠባጥባሉ፤ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ፤ በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ፤ ከእግዚአብሔርም ቤት ምንጭ ትፈልቃለች፤ የሰኪኖንንም ሸለቆ ታጠጣለች።
“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ቤት አነሣለሁ፤ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፤ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።
በዚያን ጊዜ እየታበዩ የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም።
በዚያም ቀን አምላካቸው እግዚአብሔር እንደ ሕዝቡ መንጋ ያድናቸዋል፣ እነርሱም ለአክሊል እንደሚሆኑ እንደ ከበሩ ድንጋዮች ይሆናሉ፥ በምድሩም ላይ ይብለጨለጫሉ።
እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ይከብራልና።”
ልብ ሁሉ ይማረክ ዘንድ ኅሊናም ለክርስቶስ ይገዛ ዘንድ በእግዚአብሔር ላይ የሚታበየውንና ከፍ ከፍ የሚለውን እናፈርሳለን።
እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።