ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ዘር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና፥ የኀይላችሁ ቀንበር ተሰብሮአልና ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።
ኢሳይያስ 11:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባሕርም በኩል በፍልስጥኤማውያን መርከቦች ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፤ የምሥራቅ ሰዎችንና ኤዶምያስን በአንድነት ይዘርፋሉ፤ በሞዓብ ላይ ቀድመው እጃቸውን ይዘረጋሉ፤ የአሞንም ልጆች ቀድመው ለእነርሱ ይታዘዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤ ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤ በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤ አሞናውያንም ይገዙላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤ ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤ በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤ አሞናውያንም ይገዙላቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱም ተባብረው በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤማውያን ላይ ይነሣሉ፤ በስተ ምሥራቅ የሚኖሩ ሕዝቦችንም ሀብት ይዘርፋሉ፤ የኤዶምንና የሞአብን ሕዝብ ድል ይነሣሉ፤ የዐሞንም ሕዝብ ለእነርሱ ታዛዦች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምዕራብም በኩል በፍልስጥኤማውያን ጫንቃ ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፥ የምሥራቅንም ልጆች በአንድነት ይበዘብዛሉ፥ በኤዶሚያስና በሞአብም ላይ እጃቸውን ይዘረጋሉ፥ የአሞንም ልጆች ለእነርሱ ይታዘዛሉ። |
ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ዘር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና፥ የኀይላችሁ ቀንበር ተሰብሮአልና ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።
አሁንም እንዲህ እላለሁ፤ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብር ከብዙ ሀብትዋ ጋር ይዋረዳል፤ በቍጥርም ጥቂት ይቀራል፤ ክብርዋም አይገኝም።
እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረፍትን ይሰጠናል፤ እህልም በመንኰራኵር ጭድም በጭቃ እንደሚበራይ እንዲሁ ሞዓብ ይረገጣል።
ለሚያዋርዱአችሁ ወዮላቸው! እናንተን ግን የሚያዋርዳችሁ የለም፤ የሚወነጅላችሁ እናንተን የሚወነጅል አይደለም፤ ወንጀለኞች ይጠመዳሉ፤ ይያዛሉም፤ ብል እንደበላው ልብስም ያልቃሉ።
በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም፥ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ። መቅሠፍትም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ኀይለኛ ፈሳሽ በቍጣ ይመጣል።
የአስጨናቂዎችሽም ልጆች እየተንቀጠቀጡ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብለሽም ትጠሪያለሽ።
ከኤዶምያስ፥ ከባሶራ የሚመጣ፥ ልብሱም የቀላ፥ የሚመካ ኀይለኛ፥ አለባበሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የምከራከር፥ ስለ ማዳንም የምፈርድ እኔ ነኝ።
ጠላቶቹን ሶርያውያንንም ከምሥራቅ፥ አረማውያንንም ከምዕራብ ያንቀሳቅስበታል፤ እስራኤልንም በተከፈተ አፍ ይበሉታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
በሞዓብና በአሞንም ልጆች መካከል፥ በኤዶምያስም፥ በምድርም ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ቅሬታ እንዳስቀረ፥ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው ሰሙ።
ስለዚህ እነሆ በአሞን ልጆች ከተማ በራባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለጥፋትም ትሆናለች፥ መንደሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር።
እነሆ እንደ ንስር ወጥቶ ይመለከታል፤ ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፤ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኀያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታቸው ስለ ቄዳርና ስለ አሦር መንግሥታት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፤ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።
በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምያስን እበቀላለሁ፤ እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴም መጠን በኤዶምያስ ያደርጋሉ፤ በቀሌንም ያውቃሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በሀገራቸው ንጹሑን ደም አፍስሰዋልና በይሁዳ ልጆች ላይ ስለ አደረጉት ግፍ ግብፅ ምድረ በዳ፥ ኤዶምያስም በረሃ ይሆናል።
ይኸውም የቀሩ ሰዎችንና ስሜም የተጠራባቸውን አሕዛብን ሁሉ ይፈልጉ ዘንድ ነው” ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።
ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው፣ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ከሩቅም ይመጣሉ፥ ለመብልም እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ።
በባሕር ዳር ለሚኖሩ ለከሊታውያን ሕዝብ ወዮላቸው! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብህም ሰው እንዳይኖር አጠፋሃለሁ።
የባሕሩም ዳር ለይሁዳ ቤት ቅሬታ ይሆናል፥ በዚያም ይሰማራሉ፣ አምላካቸው እግዚአብሔር ይጐበኛቸዋልና፥ ምርኮአቸውንም ይመልሳልና በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ ማታ ይተኛሉ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፥ የሳማ ስፍራና የጨው ጕድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፣ የሕዝቤም ቅሬታ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።
አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እባርከዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፤ ከእስራኤልም ሰው ይነሣል፥ የሞዓብንም አለቆች ይመታል፤ የሤትንም ልጆች ሁሉ ይማርካል።
የእስራኤልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያንና አማሌቃውያን ይዘምቱባቸው ነበር፥ በምሥራቅም የሚኖሩ ልጆች አብረው ይዘምቱባቸው ነበር፤