Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሶፎንያስ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በባሕር ዳር ለሚኖሩ ለከሊታውያን ሕዝብ ወዮላቸው! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብህም ሰው እንዳይኖር አጠፋሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፣ የከሊታውያን ሰዎች ሆይ፤ ወዮላችሁ! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፤ በአንቺ ላይ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ “ፍጹም አጠፋሻለሁ፤ ከነዋሪዎችሽም የሚተርፍ የለም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እናንተ በባሕር ዳር የምትኖሩ፥ የከሪታውያን ሕዝብ ወዮላችሁ! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የጌታ ቃል በእናንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብሽ እንዳይኖር አድርጌ አጠፋሻለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እናንተ በባሕር ዳር የምትኖሩ ከሪታውያን ማለት ፍልስጥኤማውያን ወዮላችሁ! የእግዚአብሔር ፍርድ በእናንተ ላይ ደርሷል፤ የፍልስጥኤም ምድር ለሆንሽው ከነዓን ወዮልሽ አንድ እንኳ ነዋሪ እንዳይኖርብሽ አድርጌ አጠፋሻለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በባሕር ዳር ለሚኖሩ ለከሊታውያን ሕዝብ ወዮላቸው! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብህም ሰው እንዳይኖር አጠፋሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሶፎንያስ 2:5
14 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እጄን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ መኳ​ን​ን​ቱ​ንም እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ የባ​ሕ​ሩ​ንም ዳር ቅሬታ አጠ​ፋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ስ​ቀ​ሎ​ናና በባ​ሕር ዳር በቀ​ሩ​ትም ቦታ​ዎች ላይ ትእ​ዛዝ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ በዚ​ያም አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ታ​ልና እን​ዴት ዝም ትላ​ለህ? በዚያ ትነ​ሣ​ለህ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ን​ተና ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ሁት ወገን ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ይህን ቃል ስሙ፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦


በግ​ብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ግዛ​ቶች ለጋዛ፥ ለአ​ዛ​ጦን፥ ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ ለጌት፥ ለአ​ቃ​ሮን፥ እን​ዲ​ሁም ለኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን በተ​ቈ​ጠ​ረ​ችው በከ​ነ​ዓን ግራ በኩል እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አቃ​ሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤


ምሳሌውንም ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አውቀዋልና ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። ትተውትም ሄዱ።


ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።


አሕዛብን አጥፍቻለሁ፣ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፣ መንገዳቸውን ማንም እንዳያልፍባት ምድረ በዳ አድርጌአለሁ፥ ከተሞቻቸውም ማንም እንዳይኖርባቸው፥ አንድስ እንኳ እንዳይቀመጥባቸው ፈርሰዋል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ና​ንተ ላይ ለሙሾ የማ​ነ​ሣ​ውን ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ድሆ​ችም በው​ስ​ጣ​ችሁ ይሰ​ማ​ራሉ፤ ድሆች ሰዎ​ችም በሰ​ላም ያር​ፋሉ፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ረኃብ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ ከእ​ና​ን​ተም የቀ​ሩት ያል​ቃሉ።


እነ​ር​ሱም አም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መኳ​ን​ንት፥ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከበ​ዓ​ል​ሄ​ር​ሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ በሊ​ባ​ኖስ ተራራ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፤


እኛም በከ​ሊ​ታ​ው​ያን አዜብ፥ በይ​ሁ​ዳም በኩል፥ በካ​ሌ​ብም አዜብ ላይ ዘመ​ትን፥ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ል​ናት” አለው።


ፍል​ስ​ጥ​ኤም ሆይ፥ ከእ​ባቡ ዘር እፉ​ኝት ይወ​ጣ​ልና፥ ፍሬ​ውም የሚ​በ​ር​ርና እሳት የሚ​መ​ስል እባብ ይሆ​ና​ልና፥ የኀ​ይ​ላ​ችሁ ቀን​በር ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ሁላ​ች​ሁም ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ።


እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፥ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ።


የቀ​ረ​ች​ውም ምድር ይህች ናት፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን፥ የጌ​ሴ​ር​ያ​ው​ያ​ንና የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ሀገር ሁሉ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios