ኢሳይያስ 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቍጣዬ በትር ለሆኑ፥ ለመዓቴም ጨንገር በእጃቸው ላለ ለአሦራውያን ወዮላቸው! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የቍጣዬ በትር ለሆነ፣ የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው ለአሦራዊው ወዮለት! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቁጣዬ በትር ለሆነ፤ የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው ለአሦራዊው ወዮለት! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የቊጣዬ በትር፥ የተግሣጼ ጨንገር የሆንከው አሦር፥ ወዮልህ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቍጣዬ በትር ለሆነ፥ የመዓቴም ጨንገር በእጁ ላለ ለአሦር ወዮለት! |
አሁን በውኑ ያለ እግዚአብሔር ትእዛዝ ይህን ስፍራ እናጠፋ ዘንድ ወጥተናልን? እግዚአብሔር፦ ወደዚች ሀገር ወጥታችሁ አጥፉአት አለን።”
“እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።
“በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይነሣልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ሰው ላይ ይጓደዳልን? ይህም ዘንግ በሚመቱበት ላይ እንደ መነሣት፥ በትርም ዕንጨት አይደለሁም እንደ ማለት ነው።”
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፥ “እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፤ እንደ መከርሁም እንዲሁ ይጸናል።
አሦርን በምድሬ ላይ እሰብረዋለሁ፤ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ ቀንበሩም ከእነርሱ ላይ ይነሣል፤ ሸክሙም ከጫንቃቸው ላይ ይወገዳል።”
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል፤ ቍጣውም ከከንፈሮቹ ቃል ክብር ጋር ይነድዳል፤ ቃሉም ቍጣን የተመላ ነው፤ የቍጣውም መቅሠፍት እንደምትበላ እሳት ናት፤
እግዚአብሔርም የድምፁን ክብር ያሰማል፤ የክንዱንም መፈራት፥ በጽኑ ቍጣና በምትበላ እሳት፥ በወጀብም፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በበረዶም ድንጋይ ይገልጣል።
የእግዚአብሔር ቍጣ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ነውና፤ መቅሠፍቱም ያጠፋቸውና ለጦር ይሰጣቸው ዘንድ በቍጥራቸው ልክ ነው።
ታያላችሁ፤ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፤ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የእግዚአብሔርም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፤ ዐላውያንንም ያጠፋቸዋል።”
እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።”
በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ ባመጣው ታላቅ ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይላጫል።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ብርቱና ብዙ የሆነውን የወንዝ ውኃ፥ የአሦርን ንጉሥና ክብሩን ሁሉ ያመጣባቸዋል፤ ወንዙም ሞልቶ ይወጣል፤ በዳሮቻቸውም ሁሉ ላይ ይፈስሳል፤
ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፤ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
“እነሆ ቀኑ ደርሶአል፤ እነሆ! የእግዚአብሔር ቀን ወጥታለች፤ ስብራትህ ደርሶአል፤ ብትርም አብባለች፤ ስድብም በዝቶአል።
አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፣ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል።