Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ናሆም 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ስለ ነነዌ የተነገረ ሸክም፣ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ስለ ነነዌ ጥፋት የተነገረ ንግር፤ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የነነዌ ሸክም፤ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ስለ ነነዌ ጥፋት ኤልቆሻዊው ናሆም የተናገረው ቃልና ያየው ራእይ የሚከተለው ነው።

Ver Capítulo Copiar




ናሆም 1:1
19 Referencias Cruzadas  

አሦ​ርም ከዚ​ያች ሀገር ወጣ፤ ነነ​ዌን፥ ረሆ​ቦት የተ​ባ​ለ​ች​ውን ከተማ ካለ​ህን፥


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ተመ​ል​ሶም በነ​ነዌ ተቀ​መጠ።


ለቍ​ጣዬ በትር ለሆኑ፥ ለመ​ዓ​ቴም ጨን​ገር በእ​ጃ​ቸው ላለ ለአ​ሦ​ራ​ው​ያን ወዮ​ላ​ቸው!


የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ በባ​ቢ​ሎን ላይ ያየው ራእይ።


ንጉሡ አካዝ በሞ​ተ​በት ዓመት ይህ ነገር ሆነ።


ስለ ሞዓብ የተ​ነ​ገረ ቃል። ሞዓብ በሌ​ሊት ትጠ​ፋ​ለች፤ የሞ​ዓ​ብም ምሽግ በሌ​ሊት ይፈ​ር​ሳል።


ስለ ግብፅ የተ​ነ​ገረ ራእይ። እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣን ደመና ተቀ​ምጦ ወደ ግብፅ ይመ​ጣል፤ የግ​ብ​ፅም የእ​ጆ​ቻ​ቸው ሥራ​ዎች በፊቱ ይዋ​ረ​ዳሉ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ልብ በው​ስ​ጣ​ቸው ይቀ​ል​ጣል።


ስለ ምድረ በዳ የተ​ነ​ገረ ቃል፤ ዐውሎ ነፋስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ፥ እን​ዲሁ ከሚ​ያ​ስ​ፈራ ሀገር ከም​ድረ በዳ ይመ​ጣል።


ስለ ጽዮን ሸለቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ ዛሬ ወደ ሰገ​ነት በከ​ንቱ መው​ጣ​ታ​ችሁ ምን ሆና​ች​ኋል?


ስለ ጢሮስ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት። የኬ​ል​ቀ​ዶን መር​ከ​ቦች ሆይ፥ አል​ቅሱ፤ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና፤ እን​ግ​ዲ​ህም ከኬ​ጤ​ዎን ሀገር አይ​መ​ጡ​ምና ማር​ከ​ውም ይወ​ስ​ዱ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


ከጥ​ንት ከእ​ኔና ከአ​ንተ በፊት የነ​በሩ ነቢ​ያት በብዙ ሀገ​ርና በታ​ላ​ላቅ መን​ግ​ሥ​ታት ላይ ስለ ሰል​ፍና ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነ​ፈ​ርም ትን​ቢት ተና​ገሩ።


“ተነ​ሥ​ተህ ወደ ታላ​ቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥ​ቶ​አ​ልና ለእ​ነ​ርሱ ስበክ።”


ነነዌ ግን ከዱሮ ዘመን ጀምራ እንደ ተከማቸ ውኃ ነበረች፣ አሁን ግን ይሸሻሉ፣ እነርሱም፦ ቁሙ፥ ቁሙ ይላሉ፥ ነገር ግን የሚመለስ የለም።


ነቢዩ ዕንባቆም ያየው ሸክም ይህ ነው።


እርሱም በሰሜን ላይ እጁን ይዘረጋል፥ አሦርንም ያጠፋል፣ ነነዌንም ባድማ፥ እንደ በረሃም ደረቅ ያደርጋታል።


የእግዚአብሔር ቃል ሸክም በሴድራክ ምድር ላይ ነው፥ በደማስቆም ላይ ያርፋል፣ የእግዚአብሔር ዓይን ወደ ሰውና ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ዘንድ ነው፣


በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos