ኢሳይያስ 10:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እንዲህ ይሆናል፤ ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ የአሦርን ንጉሥ የኵሩ ልብን ፍሬ፥ የዐይኑንም ከፍታ ትምክሕት ይቀጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፣ እንዲህ ይላል፤ “የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፤ እንዲህ ይላል የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “በኢየሩሳሌምና በጽዮን ተራራ የማደርገውን ሁሉ ከፈጸምኩ በኋላ ስለ ትምክሕቱና ስለ ትዕቢቱ ሁሉ ብዛት የአሦርንም ንጉሠ ነገሥት ደግሞ እቀጣለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እንዲህ ይሆናል፥ ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ የአሦርን ንጉሥ የኩሩ ልብ ፍሬን የዓይኑንም ከፍታ ትምክሕት ይጎበኛል። |
የትዕቢተኞች ሰዎች ዐይኖች ይዋረዳሉ፤ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፤ እነርሱም ይዋረዳሉ፤
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፤ ይህም ኀጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ሕዝብ በድጋሚ እንዲፈልስ አደርጋለሁ፤ አፈልሳቸዋለሁም፤ የጥበበኞችንም ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እሰውራለሁ።”
ለሚያዋርዱአችሁ ወዮላቸው! እናንተን ግን የሚያዋርዳችሁ የለም፤ የሚወነጅላችሁ እናንተን የሚወነጅል አይደለም፤ ወንጀለኞች ይጠመዳሉ፤ ይያዛሉም፤ ብል እንደበላው ልብስም ያልቃሉ።
የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማንን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግህበት፥ ዐይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን?
የተቈጣኸው ቍጣና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ሰለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።
እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ፥ የእሳትንም ነበልባል ከፍ ያደረጋችሁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ብርሃንና ባነደዳችሁት ነበልባል ሂዱ፤ ስለ እኔ ይህ ይሆንባችኋል፤ በኀዘንም ትተኛላችሁ።
በተራሮችም ላይ ስላጠኑ፥ በኮረብቶችም ላይ ስለ አሽሟጠጡኝ ስለዚህ አስቀድመው የሠሩትን ሥራቸውን በብብታቸው እሰፍራለሁ።
እነሆ ስሜ የተጠራባትን ከተማ አስጨንቃት ዘንድ እጀምራለሁ፤ በውኑ እናንተ መንጻትን ትነጻላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና አትነጹም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የአሦርን ንጉሥ እንደ ተበቀልሁ እንዲሁ እነሆ የባቢሎንን ንጉሥና ምድሩን እበቀላለሁ።
አንቺ ትዕቢተኛ ሆይ!፥ ትደክሚያለሽ፤ ትወድቂያለሽም፤ የሚያነሳሽም የለም፤ በዛፎችሽ ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያሽ ያለውንም ሁሉ ትበላለች።”
“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቁመትህ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ ራስህም በደመናት መካከል ደርሶአልና፤ ትዕቢቱንም አየሁ፤
በውኃው አጠገብ ያሉ የዕንጨቶች ሁሉ ቁመት እንዳይረዝም ራሱም ወደ ደመና እንዳይደርስ ያንም ውኃ የሚጠጡት እንጨቶች ሁሉ በርዝመታቸው ከእርሱ ጋራ እንዳይተካከሉ ሁሉም ወደ መቃብር በሚወርዱ ሰዎች መካከል በጥልቅ ምድር ሞቱ።
ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም እንዳይሉ፥ በቍጣ ጠላት ሆኑኝ።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?