Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 76:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የድ​ሮ​ውን ዘመን ዐሰ​ብሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን ዓመ​ታት ዐሰ​ብሁ፤ አነ​በ​ብ​ኹም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ልበ ሙሉ የሆኑት ተዘርፈዋል፤ አንቀላፍተውም ተኝተዋል፤ ከኀያላኑም መካከል፣ እጁን ማንቀሳቀስ የቻለ የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አንተ በዘለዓለም ተራሮች ሆነህ በድንቅ ታበራለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ጀግኖች ወታደሮች የማረኩትን ተቀሙ፤ እጃቸውንም ማንሣት አቅቶአቸው የመጨረሻ እንቅልፍ አንቀላፉ

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 76:5
10 Referencias Cruzadas  

ሁሉ ተስ​ተ​ካ​ክሎ በአ​ን​ድ​ነት ዐመፀ፤ በጎ ነገ​ርን የሚ​ሠ​ራት የለም፤ አን​ድም እንኳ የለም።


አሦ​ርም ይወ​ድ​ቃል፤ የሚ​ወ​ድ​ቀ​ውም በሰው ሰይፍ አይ​ደ​ለም፤ የም​ት​በ​ላ​ቸ​ውም የሰው ሰይፍ አይ​ደ​ለ​ችም፤ የሚ​ሸ​ሹም ከሰ​ይፍ ፊት አይ​ደ​ለም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸው ግን ይሸ​ነ​ፋሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድ​ኖች ሆነው አገ​ኙ​አ​ቸው።


እና​ንተ ከጽ​ድቅ የራ​ቃ​ችሁ ልበ ጥፉ​ዎች፥ ስሙኝ፤


በሞ​ቃ​ቸው ጊዜ እን​ዲ​ዝሉ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም እን​ቅ​ልፍ እን​ዲ​ተኙ መጠ​ጥን አጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አሰ​ክ​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ ከዚ​ያም በኋላ አይ​ነ​ቁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ እረኞችህ አንቀላፍተዋል፣ መኳንንቶችህም ዐርፈዋል፣ ሕዝብህም በተራሮች ላይ ተበትኖአል፥ የሚሰበስበውም የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos