Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 27:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በውኑ የመ​ቱ​ትን እንደ መታ እን​ዲሁ እር​ሱን መታ​ውን? ወይስ እነ​ርሱ እንደ ተገ​ደ​ሉ​በት መገ​ደል እርሱ ተገ​ድ​ሎ​አ​ልን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የመቷትን እንደ መታቸው፣ እግዚአብሔር እርሷንስ መታትን? የገደሏትን እንደ ገደላቸው፣ እርሷስ ተገደለችን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በውኑ የመቱትን እንደ መታ እንዲሁ እርሱን መታውን? ወይስ እነርሱ እንደ በተገደሉበት አገዳደል እርሱ ተገድሏል?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እስራኤል የተቀጣችው ጠላቶችዋ በእግዚአብሔር የተቀጡትን ያኽል አይደለም፤ የጠላቶችዋንም ያኽል ብዙ ሰው አልተገደለባትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በውኑ የመቱትን እንደ መታ እንዲሁ እርሱን መታውን? ወይስ እነርሱ እንደ ተገደሉበት መገደል እርሱ ተገድሎአልን? ነዳቸው ሰደዳቸው ቀሰፋቸው፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 27:7
17 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ጌታ ሥራ​ውን ሁሉ በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ በፈ​ጸመ ጊዜ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የኵሩ ልብን ፍሬ፥ የዐ​ይ​ኑ​ንም ከፍታ ትም​ክ​ሕት ይቀ​ጣል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ብር​ሃን እንደ እሳት ይሆ​ናል፤ በሚ​ነ​ድድ እሳ​ትም ይቀ​ድ​ሰ​ዋል፤ ዛፉ​ንም እንደ ሣር ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


በመ​ሸም ጊዜ ሳይ​ነጋ ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ያን​ጊ​ዜም የይ​ሁዳ ወገ​ኖች “ይህ የወ​ራ​ሾች ርስት ነው፤ የበ​ዘ​በ​ዙ​ንም ዕድል ፋንታ ይህ ነው” ይላሉ።


ኤፍ​ሬም የሚ​ጠ​ጋ​በት ምሽግ አይ​ኖ​ርም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ ንጉሥ በደ​ማ​ስቆ አይ​ነ​ግ​ሥም። የሶ​ርያ ቅሬታ ሆይ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከክ​ብ​ራ​ቸው የም​ት​ሻል አይ​ደ​ለ​ህም” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አሦ​ርም በመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ከመ​ታው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድምፅ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣል።


አሦ​ርም ይወ​ድ​ቃል፤ የሚ​ወ​ድ​ቀ​ውም በሰው ሰይፍ አይ​ደ​ለም፤ የም​ት​በ​ላ​ቸ​ውም የሰው ሰይፍ አይ​ደ​ለ​ችም፤ የሚ​ሸ​ሹም ከሰ​ይፍ ፊት አይ​ደ​ለም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸው ግን ይሸ​ነ​ፋሉ።


ዓለ​ትም ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች ድልም ይሆ​ናሉ የሸ​ሸም ይያ​ዛል። በጽ​ዮን ዘርእ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቤቶች ያሉት ብፁዕ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ከተ​ሞች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዲሁ ሰው በዚያ አይ​ቀ​መ​ጥም፤ የሰ​ውም ልጅ አይ​ኖ​ር​ባ​ትም።


በጽ​ዮን በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ በባ​ቢ​ሎ​ንና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግዚአብሔርም ከስምህ ማንም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይዘራ ስለ አንተ አዝዞአል፣ ከአምላኮችህ ቤት የተቀረጸውንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል አጠፋለሁ። አንተም የተጠቃህ ነህና መቃብርህን እምሳለሁ።


ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos