Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የኤ​ፍ​ሬም ሕዝብ ሁሉና በሰ​ማ​ርያ የሚ​ኖሩ ያው​ቃሉ፤ በት​ዕ​ቢ​ትና በልብ ኵራ​ትም እን​ዲህ ይላሉ፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሕዝቡ በሙሉ፣ ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች ይህን ያውቃሉ፤ በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጡቦቹ ወድቀዋል፤ እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤ የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤ እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የእስራኤል ሕዝብና በሰማርያ ከተማም የሚኖሩ ሁሉ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር መሆኑን ያውቃሉ፤ ሆኖም፥ ትዕቢተኞችና እልኸኞች ሆነው እንዲህ ይላሉ፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9-10 በትዕቢትና በልብ ኵራት፦ ጡቡ ወድቆአል፥ ነገር ግን በተወቀረ ድንጋይ እንሰራለን፥ የሾላ ዛፎች ተቈርጠዋል፥ ነገር ግን ዝግባን እንተካባቸዋለን የሚሉ በኤፍሬምና በሰማርያ የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 9:9
23 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ ከጽ​ድቅ የራ​ቃ​ችሁ ልበ ጥፉ​ዎች፥ ስሙኝ፤


እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ቃላችሁ በእኔ ላይ ድፍረት ሆኖአል፥ ይላል እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ በአንተ ላይ ደፍረን የተናገርነው በምንድር ነው? ብላችኋል።


እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ይላሉ፦ እነሆ ይህ ይመ​ጣል፤ በመ​ጣም ጊዜ እነ​ርሱ ነቢይ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ነበረ ያው​ቃሉ።”


እን​ዲሁ በግ​ብፅ ላይ ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


ንጉ​ሡም ያለ​ቅ​ሳል፥ አለ​ቃም ውር​ደ​ትን ይለ​ብ​ሳል፤ የም​ድ​ርም ሕዝብ እጅ ትሰ​ላ​ለች፤ እንደ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም መጠን አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በፍ​ር​ዳ​ቸ​ውም መጠን እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅር አል​ልም፤ መን​ገ​ድ​ሽ​ንም አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ርኵ​ሰ​ት​ሽም በመ​ካ​ከ​ልሽ ነው፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ቀ​ሥፍ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


አሕ​ዛ​ብም መጥ​ተው ይህ​ችን ሀገር ያዟት፤ ይህ​ችም ከተማ ከረ​ኃ​ቡና ከጦሩ የተ​ነሣ በወ​ጓት በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች እጅ ወደ​ቀች፤ እንደ ተና​ገ​ር​ኸ​ውም ሆነ።


አንተ እል​ከኛ፥ አን​ገ​ት​ህም የብ​ረት ጅማት፥ ግን​ባ​ር​ህም ናስ እንደ ሆነ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤


አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክን​ድ​ህን አላ​ወ​ቁም፤ ካወቁ ግን ያፍ​ራሉ። አላ​ዋ​ቆች ሰዎ​ችን ቅን​አት ያዛ​ቸው፤ አሁ​ንም እሳት ጠላ​ቶ​ችን ትበ​ላ​ለች።


ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ።


ሚክ​ያ​ስም፥ “እነሆ፥ በዚያ ቀን ልት​ሸ​ሸግ ወደ ውስ​ጠ​ኛው እል​ፍ​ኝህ በሄ​ድህ ጊዜ ታያ​ለህ” አለ።


ለዳ​ዊት ቤትም፥ “አራም ከኤ​ፍ​ሬም ጋር ተባ​ብ​ረ​ዋል” የሚል ወሬ ተነ​ገረ፤ የእ​ር​ሱም ልብ የሕ​ዝ​ቡም ልብ የዱር ዛፍ በነ​ፋስ እን​ደ​ሚ​ና​ወጥ ተና​ወጠ።


ጌታ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ሞትን ላከ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ወደቀ።


ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል፥ ያለ ወይን ጠጅ ለሰ​ከሩ፥ በወ​ፍ​ራም ተራራ ራስ ላይ ላለ​ችም ለረ​ገ​ፈች ለክ​ብር ጌጥ አበባ ወዮ!


የኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል በእ​ጅና በእ​ግር ይረ​ገ​ጣል፤


እስ​ራ​ኤል ፈጣ​ሪ​ውን ረስ​ቶ​አል፤ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​ንም ሠር​ቶ​አል፤ ይሁ​ዳም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች አብ​ዝ​ቶ​አል፤ እኔ ግን በከ​ተ​ሞች ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትበ​ላ​ለች።


ኤዶምያስ፦ እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፣ በሰዎችም ዘንድ፦ የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios