ኤዶምያስን በእውነት መታህ፤ ልብህንም ከፍ ከፍ አደረግህ፤ በዚያ ተመካ፤ በቤትህም ተቀመጥ፤ አንተ፥ ይሁዳም ከአንተ ጋር ትወድቁ ዘንድ ስለ ምን መከራን ትሻለህ?” ብሎ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ላከ።
ዕንባቆም 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ አታላይና ኵሩ ሰው ነው፣ በስፍራው ዐርፎ አይቀመጥም፣ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፣ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ የወይን ጠጅ አታልሎታል፤ ትዕቢተኛ ነው፤ ከቶ አያርፍም፤ እንደ መቃብር ስስታም ነው፣ እንደ ሞት ከቶ አይጠግብም፤ ሕዝቦችን ለራሱ ይሰበስባል፤ ሰዎችንም ሁሉ ማርኮ ይወስዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርግጥ ወይን አታላይ ነው፤ ትዕቢተኛ ሰው በስፍራው አርፎ አይቀመጥም፤ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፤ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርግጥ ሀብት ሰውን ያታልላል፤ ትምክሕተኛ ሰው ዕረፍት የለውም፤ እንደ መቃብር ስስታም እንደ ሞትም በቃኝ የማይል ስለ ሆነ መንግሥታትን ሁሉ ለራሱ ይወራል፤ ሕዝቦችንም ይማርካል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ አታላይና ኵሩ ሰው ነው፥ በስፍራው ዐርፎ አይቀመጥም፥ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፥ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል። |
ኤዶምያስን በእውነት መታህ፤ ልብህንም ከፍ ከፍ አደረግህ፤ በዚያ ተመካ፤ በቤትህም ተቀመጥ፤ አንተ፥ ይሁዳም ከአንተ ጋር ትወድቁ ዘንድ ስለ ምን መከራን ትሻለህ?” ብሎ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ላከ።
የሞዓብን ትዕቢትና እጅግ መኵራቱን ሰምተናል፤ ትዕቢቱንም አስወገድሁ፤ ጥንቈላህ እንዲህ አይደለምና፥ እንዲህም አይደለም፤
ሲኦልም ሆድዋን አስፍታለች፤ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፤ የተከበሩና ታላላቅ ሰዎች ባለጠጎቻቸውና ድሆቻቸውም ወደ እርስዋ ይወርዳሉ።
ከጎረቤቶቻቸው እርሻ ይወስዱ ዘንድ፥ ምድርንም ለብቻቸው ይይዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ፥ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!
እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
“ቀስትን የሚገትሩ ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት፤ ከእርስዋም ሰዎች አንድ አያምልጥ፤ የእስራኤልን ቅዱስ እግዚአብሔርን ተቃውማለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፤ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።
በሞቃቸው ጊዜ እንዲዝሉ፥ የዘለዓለምም እንቅልፍ እንዲተኙ መጠጥን አጠጣቸዋለሁ፤ አሰክራቸዋለሁም፤ ከዚያም በኋላ አይነቁም፥ ይላል እግዚአብሔር።