ዘፍጥረት 49:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፥ “በኋለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን ሁሉ አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በኋለኛው ዘመን ምን እንደሚደርስባችሁ እነግራችሁ ዘንድ ተሰብሰቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ “በኋለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብስቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአንድነት ተሰብሰቡና ወደ ፊት የሚገጥማችሁን ነገር ልንገራችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ በኍለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብስቡ። |
በኋላ ዘመን እንዲህ ይሆናል፤ የእግዚአብሔር ቤት በተራሮች ራስ ላይ ይታያል፤ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛቡም ሁሉ ወደ እርሱ ይመጣሉ።
ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰማ፥ “እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አያስቀሩልህም፤ ይላል እግዚአብሔር።
ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ይሰማሉ፤ ይህን ማን ነገራቸው? አንተን በመውደድ የከለዳውያንን ዘር አስወግድ ዘንድ ፈቃድህን በባቢሎን ላይ አደረግሁ።
በመጨረሻውም ዘመን የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።
አሁንም፥ እነሆ፥ ወደ ሕዝቤ እሄዳለሁ፤ ና፥ ይህ ሕዝብ በኋለኛው ዘመን በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን እነግርሃለሁ።”
በኋለኛዪቱ ቀን እንዲህ ይሆናል ይላል እግዚአብሔር፦ ሥጋን በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈስሳለሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፤ ጐልማሶቻችሁ ራእይን ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ።
ይሰሙና ይማሩ ዘንድ፥ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ይፈሩ ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ሰምተው ያደርጉ ዘንድ ሕዝቡን ወንዶችና ሴቶችን፥ ሕፃኖቻችሁንም፥ በሀገራችሁ ደጅ ያለውንም መጻተኛ ሰብስብ።
ይህም ሁሉ ነገር በመጨረሻው ዘመን ይደርስብሃል፤ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔርም ትመለሳለህ፤ ቃሉንም ትሰማለህ።
መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥
ከዚያ በኋላም አየሁ፤ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ፤” አለ።