Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 4:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚያ በኋላም አየሁ፤ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህ በኋላ እነሆ፤ በሰማይ የተከፈተ በር አየሁ፤ ቀደም ሲል እንደ መለከት ሲናገረኝ የሰማሁት ድምፅ፣ “ወደዚህ ና፤ ከዚህም በኋላ ሊሆን የሚገባውን ነገር አሳይሃለሁ” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከዚያ በኋላም አየሁ፤ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ! እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ መሆን ያለበትን ነገር አሳይሃለሁ፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እነሆ በሰማይ የተከፈተ በር ነበር፤ በመጀመሪያ ሰምቼው የነበረው እንደ እምቢልታ ያለው ድምፅ እንዲህ አለ፦ “ና ወደዚህ ውጣ፤ ወደፊት መሆን የሚገባቸውን ነገሮች አሳይሃለሁ፤”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 4:1
21 Referencias Cruzadas  

በሰማይም “ወደዚህ ውጡ” የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ በዚ​ያም ሁን፤ እኔ የጻ​ፍ​ሁ​ትን ሕግና ትእ​ዛዝ፥ የድ​ን​ጋ​ይም ጽላት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ሕግ​ንም ትሠ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።


እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


ወዲያውም ከውሃው በወጣ ጊዜ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርድበት አየና “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፤


እርሱም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፤ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።”


ሰባተኛውም ጽዋውን በአየር ውስጥ አፈሰሰ፤ ከመቅደሱም ውስጥ “ተፈጽሞአል!” የሚል ታላቅ ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ።


“እነሆ ሰማይ ተከ​ፍቶ፤ የሰው ልጅም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ቆሞ አያ​ለሁ” አለ።


ያ የእ​ው​ነት መን​ፈስ በመጣ ጊዜ ግን ወደ እው​ነት ሁሉ ይመ​ራ​ች​ኋል፤ የሚ​ሰ​ማ​ውን ሁሉ ይና​ገ​ራል እንጂ እርሱ ከራሱ አይ​ና​ገ​ር​ምና፤ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ከተ​ጠ​መቁ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ተጠ​መቀ፤ ሲጸ​ል​ይም ሰማይ ተከ​ፈተ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሂድ፤ ውረድ፤ አንተ አሮ​ንም ከአ​ንተ ጋር ትወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ካህ​ና​ቱና ሕዝቡ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወጡ ዘንድ አይ​ደ​ፋ​ፈሩ” አለው።


ሰማ​ይም ተከ​ፍቶ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን የተ​ያዘ እንደ ታላቅ መጋ​ረጃ ያለ ዕቃ ወደ ምድር ሲወ​ርድ አየ።


ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኀ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤


ከአ​ባ​ታ​ቸው ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሰው ሁሉ ከቤተ ሰቡ ጋር ገባ፤


በሠ​ላ​ሳ​ኛው ዓመት በአ​ራ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን በኮ​ቦር ወንዝ በም​ር​ኮ​ኞች መካ​ከል ሳለሁ ሰማ​ያት ተከ​ፈቱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ራእይ አየሁ።


የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየሁ፤


በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።


ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios