ከዚያም ሄደ፤ የሣፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን በዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎች ሲያርስ፥ እርሱም ከዐሥራ ሁለተኛው ጋር ሆኖ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ አልፎ መጐናጸፊያውን ጣለበት።
ዘፀአት 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የአማቱን የምድያምን ካህን የዮቶርን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ በጎቹንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ቀን ሙሴ የምድያም ካህን የሆነውን የዐማቱን የዮቶር በጎችና ፍየሎች እየጠበቀ ሳለ፣ መንጋውን እየነዳ ወደ ምድረ በዳው ዳርቻ አምርቶ የእግዚአብሔር ተራራ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ኮሬብ ቀረበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የምድያን ካህን የሆነውን የአማቹን የይትሮን በጎች ያሰማራ ነበር፤ በጎቹን ከምድረ በዳው ማዶ ነዳቸው፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ ሙሴ የምድያም ካህን የሆነውን የዐማቹን የየትሮንን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ መንጋውንም እየነዳ ከበረሓው ማዶ ወዳለው የእግዚአብሔር ተራራ እየተባለ ወደሚጠራው ወደ ሲና መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የአማቱን የምድያምን ካህን የዮቶርን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ ወደ ምድረ በዳ ዳርቻም በጎቹን ነዳ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ። |
ከዚያም ሄደ፤ የሣፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን በዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎች ሲያርስ፥ እርሱም ከዐሥራ ሁለተኛው ጋር ሆኖ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ አልፎ መጐናጸፊያውን ጣለበት።
እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፤ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል” አለው። ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት እንዲሁ አደረገ።
የሙሴ አማት ዮቶርም የሚቃጠል መሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እንጀራ ሊበሉ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ።
በሦስተኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጅተው ይጠብቁ።
ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ እግዚአብሔርም ከተራራው ጠርቶ አለው፥ “ለያዕቆብ ቤት እንዲህ በል፤ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ንገር፤
ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ይጠብቁ ነበር፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ሊያጠጡ የውኃዉን ገንዳ ሞሉ።
እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፤ እንዲህ ሲል፥ “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ይህ ለአንተ ምልክት ይሆንሃል፤ ሕዝቡን ከግብፅ በአወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታመልካላችሁ” አለው።
ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶርም ተመለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕይወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወንድሞች እሄዳለሁ” አለው። ዮቶርም ሙሴን፥ “በደኅና ሂድ” አለው።
እግዚአብሔርም አሮንን አለው፥ “ሄደህ በምድረ በዳ ሙሴን ተገናኘው፤” ሄዶም በእግዚአብሔር ተራራ ተገናኘው፤ እርስ በርሳቸውም ተሳሳሙ።
በቴቁሔ በላም ጠባቂዎች መካከል የነበረ አሞጽ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከሆነበት ከሁለት ዓመት በፊት ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ቃል ይህ ነው።
ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፥ “እግዚአብሔር፦ ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን፤ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን” አለው።
ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድሩበትን ቦታ ታገኝላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ትቀድማቸው ነበር።
“አርባ ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ በበረሃ በደብረ ሲና የእግዚአብሔር መልአክ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስባቸው፤ እነርሱ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩና ለልጆቻቸውም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎኛልና በኮሬብ በተሰበሰባችሁ ጊዜ በፈጣሪያችሁ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ቆማችሁ ንገራቸው።
ቄናዊውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኢዮባብ ልጆች ከቄናውያን ተለይቶ ድንኳኑን በቃዴስ አጠገብ እስከ ነበረው ታላቅ ዛፍ ድረስ ተከለ።
ሳሙኤልም እሴይን፥ “ልጆችህ እኒህ ብቻ ናቸው?” አለው። እርሱም፥ “ታናሹ ገና ቀርቶአል፤ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል” አለ። ሳሙኤልም እሴይን፥ “እርሱ እስኪመጣ ድረስ ለማዕድ አንቀመጥምና ልከህ አስመጣው” አለው።