Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ለም​ድ​ያ​ምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም የዮ​ቶ​ርን በጎች ይጠ​ብቁ ነበር፤ እነ​ር​ሱም መጥ​ተው ውኃ ቀዱ፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም የዮ​ቶ​ርን በጎች ሊያ​ጠጡ የው​ኃ​ዉን ገንዳ ሞሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ውሃው ጕድጓድ መጥተው የአባታቸውን በጎች ውሃ ለማጠጣት ገንዳውን ሞሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፥ የአባታቸውንም በጎች ሊያጠጡ የውሀውን ገንዳ ሞሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 አንድ የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ውሃ ለመቅዳትና በገንዳ እየሞሉ የአባታቸውን በጎችና ፍየሎች ለማጠጣት ወደዚያ መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም በጎች ሊያጠጡ የውኃውንም ገንዳ ሞሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 2:16
11 Referencias Cruzadas  

ሙሴም የአ​ማ​ቱን የም​ድ​ያ​ምን ካህን የዮ​ቶ​ርን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር፤ በጎ​ቹ​ንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።


ሲመ​ሽም ውኃ ቀጂ​ዎች ውኃ ሊቀዱ በሚ​መ​ጡ​በት ጊዜ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ውጪ በውኃ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ግመ​ሎ​ቹን አሳ​ረፈ።


በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቈነ​ጃ​ጅት ውኃ ሊቀዱ ሲወጡ አገ​ኙና፥ “ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ?” አሉ​አ​ቸው።


ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ስም “እስ​ፍ​ን​ቶ​ፎ​ኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ የም​ት​ሆን አስ​ኔ​ት​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።


የሳ​ሌም ንጉሥ መልከ ጼዴ​ቅም እን​ጀ​ራ​ንና የወ​ይን ጠጅን አወጣ፤ እር​ሱም የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህን ነበረ።


እነሆ፥ በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ቆሜ​አ​ለሁ፤ የከ​ተ​ማዋ ሰዎች ሴቶች ልጆ​ችም ውኃ​ውን ሊቀዱ ይወ​ጣሉ፤


በተ​መ​ለ​ከ​ተም ጊዜ በሜ​ዳው እነሆ ጕድ​ጓ​ድን አየ፤ በዚ​ያም ሦስት የበ​ጎች መን​ጎች በላዩ ተመ​ስ​ገው ነበር፤ ከዚ​ያች ጕድ​ጓድ በጎ​ቹን ያጠጡ ነበ​ርና፤ በጕ​ድ​ጓ​ድ​ዋም አፍ ታላቅ ድን​ጋይ ነበ​ረች።


የም​ድ​ያም ካህን የሙሴ አማት ዮቶር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙ​ሴና ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ እንደ አወጣ ሰማ።


የሙሴ አማት ዮቶ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወሰደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እን​ጀራ ሊበሉ አሮ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ መጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios