Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለሙሴ በእ​ሳት ነበ​ል​ባል በቍ​ጥ​ቋጦ መካ​ከል ታየው፤ እነ​ሆም፥ ቍጥ​ቋ​ጦው በእ​ሳት ሲነ​ድድ፥ ቍጥ​ቋ​ጦ​ውም ሳይ​ቃ​ጠል አየ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቍጥቋጦው ውስጥ በሚንቀለቀል የእሳት ነበልባል መካከል ተገለጠለት። ሙሴም ቍጥቋጦው በእሳት ቢያያዝም እንኳ፣ አለመቃጠሉን አየ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የጌታም መልአክ በእሳት ነበልባል በቁጥቋጦው መካከል ታየው፤ ቁጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቁጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቊጥቋጦ ውስጥ በተቀጣጠለ የእሳት ነበልባል መካከል ሆኖ ተገለጠለት፤ ሙሴም ቊጥቋጦው በእሳት ተያይዞ ሳለ ምንም አለመቃጠሉን ተመለከተና፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቁጥቍጦው መካከል ታየው፤ እነሆም ቍጥቍጦው በእሳት ሲነድድ ቁጥቍጦውም ሳይቃጠል አየ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 3:2
29 Referencias Cruzadas  

በውኃ ውስጥ ባለ​ፍህ ጊዜ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ ወን​ዞ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​ህም፤ በእ​ሳ​ትም ውስጥ በሄ​ድህ ጊዜ አት​ቃ​ጠ​ልም፤ ነበ​ል​ባ​ሉም አይ​ፈ​ጅ​ህም።


ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔር ‘እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤’ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?


በየ​ወ​ቅ​ቱም ከም​ድ​ሪቱ ምላት፥ በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ውስጥ ከነ​በ​ረው በረ​ከት፥ በዮ​ሴፍ ራስ ላይ፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም በከ​በ​ረው በእ​ርሱ ራስ ላይ ይው​ረድ።


ሙታን እን​ደ​ሚ​ነ​ሡስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ‘እኔ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ’ ብሎ በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ዘንድ እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው ሙሴ ተና​ግ​ሮ​አል።


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኛም አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​አ​ክም አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ራሱ ያድ​ና​ቸ​ዋል እንጂ። እርሱ ይወ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና፥ ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ል​ምና እርሱ ተቤ​ዣ​ቸው፤ ተቀ​በ​ላ​ቸ​ውም፤ በዘ​መ​ና​ቸ​ውም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አከ​በ​ራ​ቸው።


ሂድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰብ​ስብ፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፦ መጐ​ብ​ኘ​ትን ጐበ​ኘ​ኋ​ችሁ፤ በግ​ብ​ፅም የሚ​ደ​ረ​ግ​ባ​ች​ሁን አየሁ፤


ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”


እና​ን​ተን ግን እንደ ዛሬው ሁሉ የር​ስቱ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስዶ ከብ​ረት እቶን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ችሁ።


ስለ ሥጋ ደካ​ማ​ነት የኦ​ሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተ​ሳ​ነው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ጢ​ኣ​ተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያች​ንም ኀጢ​አት በሥ​ጋው ቀጣት።


ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።


ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ፃ​ኑን ጩኸት ሰማ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከሰ​ማይ አጋ​ርን እን​ዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​ጅ​ሽን ድምፅ ባለ​በት ስፍራ ሰም​ቶ​አ​ልና አት​ፍሪ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ጠራና፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ።


“በመ​ን​ገድ ይጠ​ብ​ቅህ ዘንድ፥ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ል​ህም ስፍራ ያገ​ባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መል​አ​ኬን በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ።


በተ​ራ​ራ​ውም ራስ ላይ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር መታ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነበረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ማኑ​ሄን፥ “ለሚ​ስ​ትህ ከነ​ገ​ር​ኋት ሁሉ ተጠ​በቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios