Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ቄና​ዊ​ውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኢ​ዮ​ባብ ልጆች ከቄ​ና​ው​ያን ተለ​ይቶ ድን​ኳ​ኑን በቃ​ዴስ አጠ​ገብ እስከ ነበ​ረው ታላቅ ዛፍ ድረስ ተከለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በዚያ ጊዜ ቄናዊው ሔቤር፣ የሙሴ ዐማች የኦባብ ልጆች ከሆኑት ከሌሎቹ ቄናውያን ተለይቶ በቃዴስ አጠገብ ጻዕናይም ከተባለ ቦታ ከሚገኘው ትልቅ ወርካ ጥግ ድንኳኑን ተክሎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በዚያን ጊዜ ቄናዊው ሔቤር፥ ዐማች የአባብ ልጆች ከሆኑት ከሌሎቹ ቄናውያን ተለይቶ በቃዴስ አጠገብ ጻዕናይም ከተባለ ቦታ ከሚገኘው ባሉጥ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተክሎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ቀኔናዊው ሔቤር የሙሴ ዐማት ከነበረው ከሆባብ ልጆች ከቄናውያን ተለየ፤ ወደ ቃዴስ ቀረብ ብሎ በጸእናይም በሚገኘው በታላቁ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተከለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ቄናዊውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኦባብ ልጆች ከቄናውያን ተለይቶ ድንኳኑን በቃዴስ አጠገብ በጻዕናይም እስከ ነበረው እስከ ትልቁ ዛፍ ድረስ ተከለ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 4:11
13 Referencias Cruzadas  

የቄ​ና​ዊው የሙሴ አማት የዮ​ባብ ልጆ​ችም ከዘ​ን​ባባ ከተማ ተነ​ሥ​ተው ከዓ​ራድ በአ​ዜብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕ​ዝቡ ጋር ተቀ​መጡ።


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከመ​ሐ​ላም፥ ከሞ​ላም፥ ከቤ​ሴ​ሜ​ይን፥ ከአ​ርሜ፥ ከና​ቦ​ቅና፥ ከኢ​ያ​ፍ​ታ​ሜን እስከ ይዳም ድረስ ነበረ፤ መው​ጫ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ነበረ።


ሙሴም የሚ​ስ​ቱን አባት የም​ድ​ያ​ማ​ዊ​ውን የራ​ጉ​ኤ​ልን ልጅ ኦባ​ብን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ለእ​ና​ንተ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ ወዳ​ለው ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እስ​ራ​ኤል መል​ካ​ምን ነገር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መል​ካ​ምን እና​ደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለን” አለው።


ቃዴስ፥ አስ​ራ​ይስ፥ የአ​ሦር ምንጭ፥


ሙሴም የአ​ማ​ቱን የም​ድ​ያ​ምን ካህን የዮ​ቶ​ርን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር፤ በጎ​ቹ​ንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።


ዲቦ​ራም ልካ ከቃ​ዴስ ንፍ​ታ​ሌም የአ​ቢኒ​ሔ​ምን ልጅ ባር​ቅን ጠርታ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዘህ አይ​ደ​ለ​ምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከዛ​ብ​ሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤


ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ማደ​ሪ​ያህ የጸ​ናች ናት፤ ጎጆ​ህም በአ​ንባ ላይ ተሠ​ር​ቶ​አል፤


የም​ድ​ያም ካህን የሙሴ አማት ዮቶር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙ​ሴና ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ እንደ አወጣ ሰማ።


ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም ወደ ራጉ​ኤል መጡ እር​ሱም፥ “ዛሬስ እን​ዴት ፈጥ​ና​ችሁ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።


የአ​ቢ​ኒ​ሔ​ምም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደ ወጣ ለሲ​ሣራ ነገ​ሩት።


ሳኦ​ልም ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቸር​ነት አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና” አላ​ቸው። ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ወጡ።


አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመ​ታ​ችሁ?” አለው፤ ዳዊ​ትም፥ “በይ​ሁዳ ደቡብ፥ በያ​ሴ​ሜጋ ደቡብ፥ በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ደቡብ ላይ ዘመ​ትን” አለው።


ከእ​ኛም ጋር ብት​ሄድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ልን መል​ካም ነገር ሁሉ እኛ ለአ​ንተ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios