ዘፀአት 28:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍርዱ ልብሰ እንግድዓም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እግዚአብሔር ፊት በሚገባበት ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆኑ ዘንድ ኡሪሙንና ቱሚሙን በደረት ኪሱ አድርግ፤ ስለዚህ አሮን ሁልጊዜ ለእስራኤላውያን የፍርድ መስጫውን በእግዚአብሔር ፊት በልቡ ላይ ይሸከማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፥ በጌታ ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በጌታ ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዑሪምና ቱሚም የተባሉትን ነገሮች በደረት ኪሱ ውስጥ ታስገባቸዋለህ፤ አሮንም ወደ ቅዱሱ ድንኳን ሲገባ በደረት ኪሱ ተሸክሞአቸው ይግባ፤ የእኔን ፈቃድ ለእስራኤል ሕዝብ ማስታወቅ ይችል ዘንድ በፊቴ ለማገልገል በሚገባበት ጊዜ ሁሉ በደረት ኪሱ ያድርጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል። |
አሮንም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ለዘለዓለም መታሰቢያ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርዱ ልብሰ እንግድዓ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸከም።
ልብሰ እንግድዓውንም በእርሱ ላይ አደረገ፤ በልብሰ እንግድዓውም ላይ የምልክትና የእውነት መገለጫዎችን አኖረበት።
እርሱ የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይሸከማል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይነግሣል፣ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፥ የሰላምም ምክር በሁለቱ መካከል ይሆናል።
በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃሉም ይግቡ።”
እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወጣለሁ፤ ስለ ሕይወታችሁም ሰውነቴን አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እናንተንም እጅግ ብወዳችሁ ራሴን ወደድሁ።
ይህንም የምለው በእናንተ ለመፍረድ አይደለም፤ ለሞትም፥ ለሕይወትም ቢሆን እናንተ በልባችን እንዳላችሁ ፈጽሜ ተናግሬአለሁና።
ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፥ ለሌዊ ቃሉን፥ በመከራም ለፈተኑት፥ በክርክር ውኃም ለሰደቡት፥ ለእውነተኛው ሰው ጽድቁን መልስ።
ስለዚህም የሕዝብን ኀጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።
ሊቀ ካህናታችን ለድካማችን መከራ መቀበልን የማይችል አይደለምና፤ ነገር ግን ከብቻዋ ከኀጢአት በቀር እኛን በመሰለበት ሁሉ የተፈተነ ነው።
ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሠራች የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ፥ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።
እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች፥ “ከነዓናውያንን የሚወጋልን ማን አለቃ ይወጣልናል?” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጠየቁ።
የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም፥ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት መሪ ሆኖ ማን ይውጣልን?” ብለው ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤
የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፤ እግዚአብሔርንም፥ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን?” ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም “በእነርሱ ላይ ውጡ” አለ።
ሳኦልም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም በሕልም አላሚዎች፥ ወይም በነጋሪዎች፥ ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።