Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ “ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን የሚ​ወ​ጋ​ልን ማን አለቃ ይወ​ጣ​ል​ናል?” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠየቁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኢያሱ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን፣ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን ቀድሞ ይውጣልን?” ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን በቅድሚያ ይወጣልናል?” ብለው ጌታን ጠየቁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ “በከነዓናውያን ላይ አደጋ ለመጣል ከነገዶቻችን መካከል ተቀዳሚ ሆኖ ማን ይዝመት?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲህም ሆነ፥ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች፦ ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን በፊት ይወጣልናል? ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 1:1
17 Referencias Cruzadas  

የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ጠይ​ቁ​ልን” አለው።


ሙሴም አማ​ቱን፥ “ሕዝቡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ ለመ​ጠ​የቅ ወደ እኔ ይመ​ጣሉ፤


በፍ​ርዱ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓም ውስጥ ኡሪ​ም​ንና ቱሚ​ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ወደ ቤተ መቅ​ደስ በገባ ጊዜ በአ​ሮን ልብ ላይ ይሆ​ናሉ፤ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሁል​ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸ​ከ​ማል።


በካ​ህ​ኑም በአ​ል​ዓ​ዛር ፊት ይቁም፤ እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ፍርድ ይጠ​ይ​ቅ​ለት፤ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃ​ሉም ይግቡ።”


ምና​ሴም የሰ​ቂ​ቶን ከተማ ቤት​ሶ​ን​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ኢቀ​ጸ​አ​ድ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የዶ​ርን ነዋ​ሪ​ዎ​ችና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የዮ​በ​ለ​ዓ​ምን ነዋ​ሪ​ዎች፥ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የመ​ጊ​ዶን ነዋ​ሪ​ዎች መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን አል​ወ​ረ​ሳ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በዚ​ያች ሀገር ይቀ​መጡ ዘንድ ጸኑ።


እኔም የነዌ ልጅ ኢያሱ ትቶ​አ​ቸው ከአ​ለፈ አሕ​ዛብ አን​ዱን ሰው እን​ኳን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከፊ​ታ​ቸው አላ​ወ​ጣም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድ​ሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሆ​ነው ሞተ።


በተ​ራ​ራ​ማዉ በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነ​ሥ​ተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “የብ​ን​ያ​ምን ልጆች ለመ​ው​ጋት መሪ ሆኖ ማን ይው​ጣ​ልን?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለ​ቀሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን?” ብለው ጠየቁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “በእ​ነ​ርሱ ላይ ውጡ” አለ።


በዚ​ያም ዘመን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በዚያ ነበ​ረ​ችና፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቁ፤


በዚ​ያም ዘመን የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ በፊቷ ይቆም ነበ​ርና። “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ው​ጣን? ወይስ እን​ቅር?” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ነገ በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ውጡ” አላ​ቸው።


ሳሙ​ኤ​ልም፦ ያ ሰው እዚህ ይመጣ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እነሆ፥ በዕቃ መካ​ከል ተሸ​ሽ​ጎ​አል” ብሎ መለሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos