Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 9:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ክር​ስ​ቶስ በእጅ ወደ ተሠ​ራች የእ​ው​ነ​ተ​ኛ​ይቱ ምሳሌ ወደ​ም​ት​ሆን ቅድ​ስት አል​ገ​ባ​ምና፥ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ፥ ወደ እር​ስዋ ወደ ሰማይ ገባ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ክርስቶስ የእውነተኛዪቱ ድንኳን ምሳሌ ወደ ሆነችውና በሰው እጅ ወደ ተሠራችው መቅደስ አልገባም፤ ነገር ግን አሁን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት ወደ እርሷ፣ ወደ ሰማይ ገባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሠራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ለመታየት ወደ እርሷ ወደ ሰማይ ገባ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ክርስቶስ የእውነተኛይቱ “መቅደስ” ምሳሌ ወደ ሆነችውና በሰው እጅ ወደተሠራችው ቅድስተ ቅዱሳን አልገባም፤ እርሱ አሁን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት ወደ ሰማይ ገባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 9:24
32 Referencias Cruzadas  

የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።


በሰ​ማይ ባለው አም​ሳል የተ​ሠ​ራው ይህ ሥራ፥ በዚህ ደም የሚ​ነጻ ከሆነ፥ ይህ ሰማ​ያዊ መሥ​ዋ​ዕ​ትስ ከዚህ ይበ​ል​ጣል።


እር​ሱም የመ​ቅ​ደ​ስና የእ​ው​ነ​ተ​ኛ​ይቱ ድን​ኳን አገ​ል​ጋይ ነው፤ እር​ስ​ዋም በሰው ሳይ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ተ​ከ​ለች ናት።


ከአብ ወጣሁ፤ ወደ ዓለ​ምም መጣሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ዓለ​ምን እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ ወደ አብም እሄ​ዳ​ለሁ።”


የላ​ይ​ኛ​ውን አስቡ፤ በም​ድር ያለ​ው​ንም አይ​ደ​ለም።


እን​ግ​ዲህ እርሱ ራሱ ካጸ​ደቀ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሰዎች የሚ​ቃ​ወ​ማ​ቸው ማነው?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከጥ​ንት ጀምሮ በቅ​ዱ​ሳን ነቢ​ያቱ አፍ እስከ ተና​ገ​ረው የመ​ደ​ራ​ጀት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀ​በ​ለው ዘንድ ይገ​ባል።


እየ​ባ​ረ​ካ​ቸ​ውም ራቃ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ይም ዐረገ።


ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።


አሮ​ንም ወደ መቅ​ደስ በገባ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስሞች በፍ​ርዱ ልብሰ እን​ግ​ድዓ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸ​ከም።


ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።


እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።


ነገር ግን ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ሰው ግዳጅ መፈ​ጸም የማ​ይ​ቻ​ለ​ውን መባና መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት የነ​በ​ረው ለዚህ ዘመን ምሳሌ ሆነ።


እነ​ር​ሱም ሙሴ ድን​ኳ​ኒ​ቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰ​ማ​ያዊ ነገር ምሳ​ሌና ጥላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ “በተ​ራ​ራው እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልህ ምሳሌ ሁሉን ታደ​ርግ ዘንድ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎት ነበ​ርና።


እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሊቀ ካህ​ናት ሆኖ ሐዋ​ር​ያ​ችን ኢየ​ሱስ ከእኛ በፊት ወደ ገባ​ባት መጋ​ረ​ጃም ውስጥ የም​ታ​ስ​ገባ ናት።


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


እን​ግ​ዲህ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበ​ረ​በት ሲያ​ርግ ብታ​ዩት እን​ዴት ይሆን?


እርሱም ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንም ይከስሰው ዘንድ በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር።


ነፍ​ሴን ተመ​ል​ክ​ተህ ተቤ​ዣት፤ ስለ ጠላ​ቶ​ችም አድ​ነኝ።


ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም የመ​ታ​ሰ​ቢያ ድን​ጋ​ዮች ይሆኑ ዘንድ ሁለ​ቱን ዕን​ቍ​ዎች በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ አሮ​ንም በሁ​ለቱ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ስማ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሸ​ከ​ማል።


“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።


በም​ድር ያለው ማደ​ሪያ ቤታ​ችን ቢፈ​ር​ስም፥ በሰ​ማይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰው እጅ ያል​ሠ​ራው ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ቤት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን።


እን​ግ​ዲህ ወደ ሰማ​ያት የወጣ ታላቅ ሊቀ ካህ​ናት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አለን፤ በእ​ርሱ በማ​መን ጸን​ተን እን​ኑር።


ፊተ​ኛ​ይ​ቱም ደግሞ የአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሥር​ዐ​ትና የዚህ ዓለም የሆ​ነው መቅ​ደስ ነበ​ራት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios