በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
ዘፀአት 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም፥ ከእንስሳም መጀመሪያ የተወለደውን ማሕፀንን የሚከፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይልኝ፤ የእኔ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከእስራኤላውያን መካከል የእናቱ የበኵር ልጅ የሆነው ማሕፀን ከፋች ሰውም ሆነ እንስሳ የእኔ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማሕፀንን የሚከፈት በኩርን ሁሉ፤ በእስራኤል ልጆች መካከል፥ ከሰውም፥ ከእንስሳም ለእኔ ቀድስልኝ፥ የእኔ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከእስራኤል ሕዝብም ሆነ ከእንስሶቹ በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእኔ መሆን ይገባዋል፤ ስለዚህ በኲር ሆኖ የተወለደውን ሁሉ ለእኔ እንዲሆን ቀድሰው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማሕፀንን የሚከፍት በኵርን ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ የእኔ ነው።” |
በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
የእህላችንንም ቀዳምያት፥ የዛፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወይኑንና የዘይቱንም ፍሬ ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ ዐሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን ዐሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።
“ከእንስሳህ የሚወለድ በኵር ሁሉ ለእግዚአብሔር ነው፤ ማንም ይለውጠው ዘንድ አይቻለውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው።
ከሰው እስከ እንስሳ ቢሆን፥ ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀመሪያ የሚወለድ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፤ ያልነጹትንም እንስሳት በኵራት ትቤዣለህ።
“እነሆ፥ እኔ በእስራኤል ልጆች ዘንድ መጀመሪያ በሚወለደው በበኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይች ወስጃለሁ፤ በእነርሱ ፋንታ ሌዋውያን ለእኔ ይሁኑ፤
በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና፤ በግብፅ ምድር በኵርን ሁሉ በመታሁ ቀን ከእስራኤል ዘንድ በኵርን ሁሉ፥ ሰውንና እንስሳን፥ ለእኔ ለይችአለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
“ላምህና በግህ የወለዱትን ተባት የሆነውን በኵራት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ፤ በበሬህ በኵራት አትሥራበት፤ የበግህንም በኵራት አትሸልት።
ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅበረ በኵርም፥ ሁሉን ወደሚገዛም ወደ እግዚአብሔር፥ ወደ ፍጹማን ጻድቃንም ነፍሳት፥